ተመድ ኖቤል ያሸነፉት የኮንጎ ዶክተር ህይወት አደጋ ላይ ነው አለ
ዶክተሩ በደህንነት ጥበቃቸው ላይ ስጋት እንዳላቸውና የ24 ሰአት ጥበቃ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸዋል
ፕሬዘዳንት ፍሌክሲ ቲሽከዲ የተደፈሩ ሴችን በማከም የተሸለሙትን ዶክተር ደህንነት ለመጠበቅ ሁሉም ነገር ይደረጋል ብለዋል
ፕሬዘዳንት ፍሌክሲ ቲሽከዲ የተደፈሩ ሴችን በማከም የተሸለሙትን ዶክተር ደህንነት ለመጠበቅ ሁሉም ነገር ይደረጋል ብለዋል
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር በዛሬው እለት እንዳለው በጦርነት ወቅት የተደፈሩ ሴቶችን በማከም የኖቤል የሰላም ሽልማት ያሸነፉት ታዋቂው የኮንጎ ዶክተር ተደጋጋሚ ዛቻ እየደረሰባቸው መሆኑንና ህይወታቸው አደጋ ላይ መውደቁን አስታውቋል፡፡
ማስፈራሪያዎቹ ወደ ዶክተር ዴኒስ ሙክዌጅና ቤተሰቦቻቸው ስልክ በመደወልና በማህበራዊ ሚዲያ የሚደርሷቸው ሲሆን ማስፈራሪያዎቹ ዶክተሩ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት በመተቸታቸው ምክያት መሆኑን ተመድ ገልጿል፡፡
የዶክተሩ ህይወት አደጋ ላይ የወደቀ ይመስላል ያሉት የሰብአዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር ሚካኤል ባችሌት በማስፈራሪያዎቹ ላይ ገለልተኛ ምርመራ እንዲካሄድ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ዶክተር ሙክዌጂ በጂናኮሎጂስትነት በየአመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶችን በሚቀበለው በፓንዚ ሆስፒታ በሰሩት ስራ በፈረንጆቹ 2018 የኖቤል የሰላም ሽልማት አግኝተዋል፡፡
ሆስፒታሉ የጎሳ ግጭት በበዛበትና የተለያዩ ሚሊሺያና የታጠቁ ቡድኖች የሚሳተፉበትና የመንግስት የመመከት ስራ በሚሰራበት በምስራቃዊ የዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ኮንጎ የሚገኝ ነው፡፡ ዶክተሩ ብዙ የግድያ ዛቻዎች ከዚህ በፊት የደረሳቸው ሲሆን በቤተሰቦቻቸው ግቢ በፈረንጆቹ 2012 የተደረገውን ግድያ ሙከራ ማምለጥ ችለው ነበር፡፡
የኮሚሺነር የባችሌት ቢሮ ቃል አቀባይ ሩፔርት ኮለቫይሌ እንደገለጹት ማስፈራሪያው የሴቶችን መብት ለመከላከል ካደረጉት ዘመቻና በደቡባዊ ኪቩ በንጹሃን ላይ የደረሰውን ጥቃት በመተቸታቸው ነው ብለዋል፡፡
ምንምእንኳን የተመድ የሰላም አስከባሪ ኃይል በሀገሪቱ ቢኖርም የኮንጎ መንግስት ለዶክተሩ ደህንነት ሙሉ ኃላፊነት እንዳለበት ገልጸዋል፡፡ ዶክተሩ በደህንነት ጥበቃቸው ላይ ስጋት እዳላቸውና የ24 ሰአት ጥበቃ አንደሚያስፈልጋቸው አስታውቀዋል፡፡
ፕሬዘዳንት ፍሌክሲ ቲሽከዲ ባለፈው ሳምንት የዶክተሩን ደህንነት ለማስጠበቅ ሁሉንም ነገር እንደሚደርጉና በዛቻው ላይ ምርመራ እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡