የአለም እድሜ ባለጸጋ የተባሉት ደቡብ አፍሪካዊ በ116 አመታቸው ሞቱ
የእድሜ ባለጸጋው በፈረንጆቹ 1918 ተከስቶ ከነበረው የስፓኒሽ ጉንፋን የተረፉ መሆናቸው ተገልጿል
ስማቸው በድንቃድንቅ መዝገብ ባይሰፍርም ሚዲያዎች ግን የአለም የእድሜ ባለጸጋ ብለዋቸዋል
ስማቸው በድንቃድንቅ መዝገብ ባይሰፍርም ሚዲያዎች ግን የአለም የእድሜ ባለጸጋ ብለዋቸዋል
የአለም የእድሜ ባለጸጋ ይሆናሉ የተባሉት ደቡብ አፍሪካዊ ሰው በ116 አመታቸው በትናንታናው እለት ህይወታቸው አልፏል፡፡ የእድሜ ባለጸጋው በፈረንጆቹ 1918 ተከስቶ ከነበረው የስፓኒሽ ጉንፋን የተረፉ መሆናቸው ተገልጿል፡፡
የፍሪዴ ብሎም ቤተሰቦች እንደገለጹት የእድሜ ባለጸጋው በታይገርበርግ ሆስፒታል ተፈጥሮአዊ በመሆነ ምክንያት መሞታቸውን አስታውቀዋል፡፡
ብሎም በታላቋ ዊንትበርግ ተራራ አቅራቢያ በምትገኘው የምስራቃዊ የኬፕ ግዛት ውስጥ አደላይዴ በተባለች የገጠር መንገር በፈረንጆቹ 1904 ነው የተወለዱት፡፡ ነገርግን በአለም የድንቃድንቅ መዝገብ ስማቸው አልሰፈረም፡፡
በመዝገቡ በረጅም እድሜ የተመዘገበው ቦብ ዊግተን የተባለ እንግሊዛዊ ሲሆን እሱም 112 አመታት ነበር መኖር የቻለው፡፡ ነገርግን የደቡብ አፍሪካ ሚዲያዎች ይፋዊ ባይሆንም ብሎምን የአለም የእድሜ ባለጸጋ ብለውታል፡፡
ብሎም ሌሎች ቤተሰቦቹ በስፓኒሽ ጉንፋን ሲሞቱ ብቸኛው መትረፍ የቻሉ ሰው ነበሩ፡፡ ብሎም ሁለቱን የአለም ጦርነቶችና የደቡብ አፍሪካን የአፓርታይድ ስርአት ማለፍም ችለው ነበር፡፡
ብሎም ጃኔት ከተባለች ሴት ጋር ለ46 አመታት በትዳር በመኖር ሶስት ልጆችን አፍተዋል፡፡ለአምስት የልጅ ልጆችም አያት መሆን ችለው ነበር፡፡