ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ተመድ በሊባኖስ-እስራኤል ድንበር ያሰፈራቸውን ሰላም አስከባሪ ጦር እንዲያስወጣ አስጠነቀቁ
አምስት የተመድ ሰላም አስከባሪ ጦር አባላት በእስራኤል ጥቃት ቆስለዋል
ተመድ በበኩሉ የእስራኤልን ማስጠንቀቂያ ውድቅ በማድረግ ጦሩን እንደማያስወጣ አስታውቋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ተመድ በሊባኖስ-እስራኤል ድንበር ያሰፈራቸውን ሰላም አስከባሪ ጦር እንዲያስወጣ አስጠነቀቁ፡፡
በመካከለኛው ምስራቅ የተጀመረው ጦርነት አንድ ዓመት ያለፈው ሲሆን ጦርነቱ በድርድር ይፈታል ቢባልም አድማሱን እያሰፋ ቀጥሏል፡፡
የሐማስ ዋነኛ አጋር ነው በሚል በእስራኤል ጥቃት የተከፈተበት የሊባኖሱ ሂዝቦላህ ከእስራኤል ጦር ጋር በምድርአ ና አየር ለይ ውጊያዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡
እስራኤል የሁዝቦላህ ተዋጊዎችን ለመግደል በሚል የከፈተችው ጥቃት ከሁለት ሺህ በላይ ንጹሃን ዜጎችን እንደገደለ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት ያስረዳል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ከ1978 ጀምሮ በእስራኤል-ሊባኖስ ድንበር ዙሪያ የሰፈረው የተመድ ሰላም አስከባሪ ጦር አባላት ቆስለዋል ተብሏል፡፡
በእስራኤል ጥቃት ቆስለዋል የተባሉት የተመድ ሰላም አስከባሪ ሀይል አሁን ደግሞ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ አስጠንቅቀዋል፡፡
ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን እስራኤል የዓለማችን ዋነኛ ስጋት ነች አሉ
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማስጠንቀቂያ መልዕክታቸው ላይ እንዳሉት የተመድ ሰላም አስከባሪ ሀይሎች አሁኑኑ ቦታውን መልቀቅ አለባቸው፣ የሂዝቦላህ ወታደሮች ሰላም አስከባሪዎችን እንደ ምሽግ እየተጠቀሙ ወታደሮቻችንን እያጠቁብን ነው ብለዋል፡፡
እስካሁን ድረስ አምስት የተመድ ሰላም አስከባሪ ጦር አባላት በእስራኤል ጦር ጥቃት ቆስለዋል የተባሉ ሲሆን በርካታ ዓለማችን ሀገራት የእስራኤልን ድርጊት አውግዘዋል፡፡
በ1978 በእስራኤል-ሒዝቦላህ መካከል ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ ተመድ ከ40 ሀገራት የተውጣጡ 10 ሺህ ገደማ ሰላም አስከባሪዎችን ወደ ስፍራው ልኳል፡፡
ተመድ በበኩሉ ከእስራኤል የቀረበለትን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ ጦሩን ከድንበር አካባቢ እንደማያስወጣ በቃል አቀባዩ በኩል አስታውቋል፡፡