እስራኤል የኢራን ኑክሌር ማብለያ እና ሌሎች ኢሊማዎችን ለመምታት የያዘችውን አቅድ መተዋ ተገለጸ
ኢራን እስራኤል በሐማስ እና ኢዝቦላህ መሪዎች ለይ ለወሰደችው ጥቃት የአጸፋ እርምጃ መውሰዷ ይታወሳል
እስራኤል በኢራን ላይ ተመሳሳይ ጥቃት እንደምትሰነዝር መዛቷ አይዘነጋም
እስራኤል የኢራን ኑክሌር ማብለያ እና ሌሎች ኢሊማዎችን ለመምታት የያዘችውን አቅድ መተዋ ተገለጸ፡፡
አንድ ዓመት ያለፈው የመካከለኛው ምስራቅ ጦርነት በየጊዜው መልኩን እየቀያየረ አሁንም እንደቀጠለ ይገኛል፡፡
ከጋዛ ወደ ሊባኖሱ ሂዝቦላህ የዞረው ይህ ጦርነት ኢራን ከሁለት ሳምንት በፊት በእስራኤል ላይ የሚሳኤል ናዳ ተኩሳለች፡፡
ከቴህራን የተተኮሱ 180 ሚሳኤሎች የከፋ ጉዳት ሳይደርሱብኝ አክሽፌያለሁ የምትለው እስራኤል በኢራን ላይ የአጸፋ እርምጃ እንደምትወስድ በወቅቱ ዝታለች፡፡
እስራኤል ልትወስድ በምትችለው የአጸፋ እርምጃ ምክንያት በርካታ ሀገራት ወደ ቴህራን እና ሌሎች የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት በረራዎችን አቋርጠዋል፡፡
እስራኤል በኢራን የኑክሌር አረር ማብለያ፣ መሪዎች እና ሌሎች መሰረተ ልማት አውታሮችን ልታጠቃ እንደምትችል በተደጋጋሚ ገልጻ ነበር፡፡
የሊባኖስ ጦር በእስራኤል እና ሄዝቦላ ጦርነት ለምን የዳር ተመልካች ሆነ?
ስሙ ያልተጠቀሰ አንድ የአሜሪካ ባለ ስልጣን እስራኤል በኢራን ላይ ልትወስድ ባሰበችው ጥቃት ዙሪያ የኢላማዎች ማስተካከያ አድርጋለች ሲል ኤንቢሲ ዘግቧል፡፡
እንደ ዘገባው ከሆነ እስራኤል የኢራን ኑክሌር ማብለያን እና መሪዎችን ለመግደል ይዛው የነበረውን እቅዷል በመተው የኢራን ነዳጅ ማውጫ መሰረተ ልማቶች ዋነኛ ኢላማ ይሆናሉ ተብሏል፡፡
የእስራኤል ባለስልጣና በጉዳዩ ዙሪያ በይፋ እስካሁን ያልተናገሩ ሲሆን በኢራን ላይ የአጸፋ እርምጃ መውሰዳቸው የማይቀር መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ኢራን በበኩሏ ከሰሞኑ ወደ መካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ዲፕሎማቶቿን በማሰማራት የአየር ክልላቸውን ለእስራኤል እንዳይፈቅዱ አስጠንቅቀዋል ተብሏል፡፡