አሜሪካ ኃይለኛውን 'ታአድ' የጸረ-የሚሳይል ስርአት ለእስራኤል የሰጠችው ለምንድነው?
የአሜሪካ መከላከያ ወይም ፔንታጎን አሜሪካ የከፍተኛ ቦታ ጸረ-ሚሳይል ስርአት (ታአድ) ለእስራኤል መስጠቷን አረጋግጧል
አሜሪካ ይህን ጸረ- ሚሳይል ስርአት ለመስጠት የወሰነችው ኢራን በእስራኤል ላይ ያደረሰችውን መጠነሰፊ የሚሳይል ጥቃት ተከትሎ ነው
አሜሪካ ኃይለኛውን 'ታአድ' የጸረ-የሚሳይል ስርአት ለእስራኤል የሰጠችው ለምንድነው?
የአሜሪካ መከላከያ ወይም ፔንታጎን አሜሪካ የከፍተኛ ቦታ ጸረ-ሚሳይል ስርአት (ታአድ) ለእስራኤል መስጠቷን አረጋግጧል።
ባለስልጣናት እንደገለጹት 'ታአድ' የእስራኤልን የአየር መከላከል አቅም ያጠናክረዋል። አሜሪካ ይህን ጸረ- ሚሳይል ስርአት ለመስጠት የወሰነችው ኢራን በእስራኤል ላይ ያደረሰችውን መጠነሰፊ የሚሳይል ጥቃት ተከትሎ ነው።
ፕሬዝደንት ባይደን የጸረ-ሚሳይል ስርአቱ ኢራን በ180 ሚሳይሎች ያደረሰችባትን ጥቃት ለመበቀል የተዘጋጀችውን እስራኤል ለመከላከል ጥቅም ላይ ይውላል ብለዋል።
አሜሪካ የጸረ- ሚሳይል ስርአቱን የላከችው ጥቅም ላይ ከሚያውሉት የአሜሪካ ወታደሮች ጋር ነው።
በእስራኤል ምድር የተወሰኑ ወታደሮች የነበሩ ቢሆንም አሁን የተላኩት 100 ወታደሮች አሜሪካ እየሰፋ ያለውን ቀጣናዊ ጦርነት እያወሳሰበችው መሆኑን ያሳያል ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪም የእስራኤልን ሚሳይል የመከላከል አቅም ምን ደረጃ ላይ እንዳለ የሚያሳይ ነው።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአብ ጋላንት እንዳሉት እስራኤል የኢራን ጥቃት "ከባድ፣ ትክክለኛ እና አስደንጋጭ" የሆነውን የበቀል እርምጃ ገና አልወሰደችም።
ቴህራን በእስራኤል ላይ የተኮሰችው በሊባኖስ የሚንቀሳቀሰውን ሄዝቦላ መሪ ሀሰን ነስረላህን ቤሩት ውስጥ በመግደሏ ምክንያት መሆኑን ገልጻለች።
የታአድ የጸረ- ሚሳይል ስርአት የተላከው በእስራኤል የአየር መከላከያ ስርአት ውስጥ የታየውን ክፍተት ለመሙላት ይሁን እስራኤል በኢራን ላይ ከፍተኛ ጥቃት እንደምታደርስ ለማመላከት የታወቀ ነገር የለም።
ፕሬዝደንት ባይደን እስራኤል በኢራን ኑክሌር ጣቢያዎች እና በነዳጅ ወይም በኃይል መሰረተልማቶች ላይ ጥቃት እንዳታደርስ ጠይቀዋል።
ያም ሆነ ይህ እስራኤል የአሜሪካን የጸረ-ሚሳይል መከላከያ ስርአት እንደምትፈልግ ያመለክታል።
እንደ ትልቁ የአሜሪካ የጦር መሳሪያ አምራች ሎክሂድ ማርቲን ከሆነ የታአድ ስርአት ባለስቲክ ሚሳይሎችን በማክሸፍ በጣም ውጥታማ ነው።
ስርአቱ ስድስት መኪና ላይ የተጠሙዱ ማስወንጨፊያዎች ያሉት ሲሆን በእያንዳንዱ ማስወንጨፋያ ላይ ደግሞ ስምንት ማክሸፊያዎች ተገጥመውለታል። የአንዱ ባትሪ ወይም ሲስተም ዋጋ አንድ ቢሊዮን ዶላር ሲሆን ለማንቀሳቀስ 100 ሰዎች ያስፈልጋሉ።
የታአድ ስርአት በጣም የሚፈልግ የጸረ-ሚሳይል መከላከያ ስርአት ነው። ዩክሬን ከሩሲያ የሚቃጣባትን የሚሳይል ጥቃት ለመከላከል በጣምት ትፈልጠዋለች።
ኢራን ከሁለት ሳምንት በፊት ያስወነጨፈችው ሚሳይል በዌስትባንክ ተመቶ ሲወድቅ አንድ ሰው ህይወቱ አልፏል። እስራኤል በአሜሪካ እገዛ የተሰሩ 'አሮው 2' እና 'አሮው 3' የተባሉ ብዙ የተወራላቸው የሚሳይል መከላከያ ስርአቶች አላት። እነዚህ የጸረ-ሚሳይል ስርአቶች ሀይፐርሶኒክ ፍጥነት ያላቸው ሲሆን ባለስቲክ ሚሳይሎችን አየር ላይ መትተው መጣል ይችላሉ።
የታአድ ድጋፍ የባይደን አስተዳደር ለእስራኤል ያለውን ቁርጠኛ ድጋፍ የሚያሳይ ነው የሚል የፖለቲካ ትርጉም ተሰጥቶታል። ከእስራኤል የወጡ ቁጥሮች እንደሚያሳዩት ከሆነ አሜሪካ ባለፈው አመት 50ሺ ቶን የጦር መሳሪያዎችን ለእስራኤል ልካለች።
ይህ በዋሽንግተን በኩል የተወሰኑ የፖሊሲ ስህተቶች መኖራቸውንም የሚያሳይ ነው።
አሜሪካ መጀመሪያ ግጭት እንዳይባባስ እና በዲፕሎማሲ መንገድ እንዲፈታ በእስራኤል እና በተቀናቃኞቿ ላይ ጫና ለማድረግ ትሞክራለች። ነገርግን ይህ የማይሳካ ከሆነ የአጋሯን እስራኤል ውሳኔ በመደገፍ ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ሽፋን ትሰጣለች።