ሄዝቦላ በደቡባዊ ሊባኖስ የእስራኤልን ድሮን መትቶ ጣለ
እስራኤል እና ሄዝቦላ በ2006 ከባድ የሚባል ጦርነት ካካሄዱ ወዲህ በጋዛ እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጎን ለጎን ከስድስት ወራት በላይ ተኩስ በመለዋወጥ ላይ ይገኛሉ
በኢራን የሚደገፈው የሊባኖሱ ሄዝቦላ ታጣቂ ቡድን በደቡባዊ ሊባኖስ ውጊያ ላይ የነበረችውን የእስራኤል ድሮን መትቶ መጣሉን ገለጸ
በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላ በደቡባዊ ሊባኖስ የእስራኤልን ድሮን መትቶ ጣለ።
በኢራን የሚደገፈው የሊባኖሱ ሄዝቦላ ታጣቂ ቡድን በደቡባዊ ሊባኖስ ውጊያ ላይ የነበረችውን የእስራኤል ድሮን መትቶ መጣሉን ገለጸ።
በአል አሺየህ አካባቢ ሰማይ ላይ ተመትታ የወደቀችው ድሮን "በአይበገሬው ህዝባችን ላይ ጦርነት ከፍታ ነበር " ሲል ቡድኑ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።
እስራኤል እና ሄዝቦላ በ2006 ከባድ የሚባል ጦርነት ካካሄዱ ወዲህ በጋዛ እየተካሄደ ካለው ጦርነት ጎን ለጎን ከስድስት ወራት በላይ ተኩስ በመለዋወጥ ላይ ይገኛሉ።
ሄዝቦላ እንደገለጸው ተመትታ የወደቀችው ድሮን ሄርሜስ 450 የተባለች እና በእስራኤሉ የጦር መሳሪያ አምራች ኢልቢት ሲስተም የተሰራች ነች።
ይህ ጦርነቱ የበለጠ ይባባሳል የሚል ስጋትን ፈጥሯል።
ሮይተርስ እንደዘገበው ከሆነ የእስራኤል እና ሀማስ ጦርነት ከተቀሰቀሰበት ከባለፈው ጥቅምት ወር ወዲህ 240 የሄዝቦላ ተዋጊዎችን እና 68 ንጹሃንን ጨምሮ 370 ሊባኖሳውያን ተገድለዋል።
በእስራኤል በኩል ደግሞ ንጹሃን እና ወታደሮችን ጨምሮ 18 እስራኤላውያን መገደላቸውን ዘገባው ጨምሮ ገልጿል።
ሄዝቦላ፣ ከእስራኤል ጋር እየተዋጋ ለሚገኘው የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ አጋርነቱን ለማሳየት በእስራኤል ላይ ጥቃት መክፈቱን መግለጹ ይታወሳል።
የጥቅምት ሰባቱን የሀማስ ጥቃት ተከትሎ እስራኤል በጋዛ እየወሰደችው ባለው መጠነሰፊ የምድር እና የአየር ጥቃት ከ32ሺ በላይ ፍልስጤማውያንን መገደላቸው የጋዛ የጤና ባለስልጣናት ተናግረዋል።