ሄዝቦላ ድሮን መትቶ መጣሉን ተከትሎ እስራኤል በምስራቅ ሊባኖስ የአየር ጥቃት አደረሰች
እስራኤል በሄዝባለ ላይ ባደረሰችው ጥቃት እስካሁን 270 ታጣቂዎች እና 50 ንጹሀን ተገድለዋል
ሄዝቦላ የእስራኤልን ድሮን መትቶ መጣሉን ተከትሎ እስራኤል በምስራቅ ሊባኖስ በሚገኙ የሄዝቦላ መሰረተልማቶች ላይ ጥቃት ማድረሷን አስታውቃለች
ሄዝቦላ ድሮን መትቶ መጣሉን ተከትሎ እስራኤል በምስራቅ ሊባኖስ የአየር ጥቃት አደረሰች።
ሄዝቦላ የእስራኤልን ድሮን መትቶ መጣሉን ተከትሎ እስራኤል በምስራቅ ሊባኖስ በሚገኙ የሄዝቦላ መሰረተልማቶች ላይ ጥቃት ማድረሷን አስታውቃለች።
የእስራኤል ጦር ባወጣው መግለጫ እንደገለጸው የጦር ጀቶች በባልቤክ ከተማ በሚገኘውን ወታደራዊ ህንጻ እና ሌሎች ሶስት መሰረተ ልማቶችን አውድመዋል።
እስራኤል ይህን ጥቃት የሰነዘረችው ሄዝቦላ እስራኤል ሰራሽ ነች ያላትን ሄርምስ900 የተሰኘችውን ድሮን በሊባኖስ የአየር ክልል ውስጥ መትቶ በመጣሉ ምላሽ ለመስጠት ነው።
ሄዝቦላ የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ በእስራኤል ላይ ጥቃት ካደረሰ ከአንድ ቀን በኋላ ነበር ከእስራኤል ጋር ተኩስ መለዋወጥ የጀመረው።
ለሀማስ አጋርነት ያሳየው ሄዝቦላ ከእስራኤል ጋር ግጭት ውስጥ መግባቱ ቀጠናዊ ውጥረት እንዲፈጠር አድርጓል።
እስራኤል በሄዝባለ ላይ ባደረሰችው ጥቃት እስካሁን 270 ታጣቂዎች እና 50 ንጹሀን ተገድለዋል።
በጥቃቱ ምክንያት ደቡባዊ ሊባኖስ 90ሺ ሰዎች የተፈናቀሉ ሲሆን ከሀገሪቱ ሰሜናዊ የድንበር ቦታዎች ደግሞ ከ96ሺ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል።
አሜሪካ እና ሌሎች ሀገራት ለእስራኤል እና ሄዝቦላ ግጭት ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ ለመፈለግ እየጣሩ ናቸው። ነገርግን ሄዝቦላ በጋዛ የተኩስ አቁም ስምምነት ካልተደረሰ ማጥቃቱን እንደማያቆም ተናግሯል።
በእስራኤል እና ሀማስ መካከል የተጀመረው ጦርነት ግማሽ አመት ያለፈው ሲሆን የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ በግብጽ፣ በኳታር እና በአሜሪካ ጥረት አየተደረገ ነው።