ካታይባ ሄዝባላ በአሜሪካ ላይ የሚሰነዝረውን ጥቃት ማቆሙን አስታወቀ
ካታይብ ሄዝቦላ ጥቃት ለማቆም የወሰነው የኢራቅ መንግስት ጉዳዩ እንዳይባባስ ባደረገው የቀናት ጥረት ነው ተብሏል
ካታይብ ሄዝቦላህ የጋዛው ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በኢራቅ እና በሶሪያ በሚገኙ የአሜሪካ ኃይሎች ላይ ለደረሱ 150 ጥቃቶች ኃላፊነቱን ወስዷ
የኢራቁ ካታይብ ሄዝባላ በአሜሪካ ላይ የሚሰነዝረውን ጥቃት ማቆሙን አስታወቀ።
የኢራን አጋር የሆነው የኢራቁ ካታይብ ሂዝቦላ በኢራቅ ላይ ሊደርስ የሚችለው አደጋ ለመከላከል በማስብ በቀጣናው ባሉ የአሜሪካ ኃይሎች ላይ የሚያደርሱትን ጥቃት ማቆሙን አስታውቀዋል።
የካታይብ ሄዝቦላ ዋና ጸኃፊ አቡ ሁሴን አል ሀሚዳዊ "በኢራቅ ላይ ውርደት እንዳይደርስ በወራሪ ኃይሎች ላይ ጥቃት ማቆማችንን ብናሳውቅም፣ በጋዛ ያለውን ህዝባችንን መከላከልላችንን እንቀጥላለን" ብለዋል።
አሜሪካ በጆርዳን ውስጥ በሶሪያ እና ኢራቅ ድንበር በሚገኘው ታወር 22 በተባለው የጦረ ሰፈር ላይ በተቃጣ ጥቃት 3 ወታደሮቿ ሲገደሉባት ሌሎች 34 ደግሞ ቆስለውባታል።
አሜሪካ ለዚህ ጥቃት እነዚህን ታጣቂዎች ተጠያቂ አድርጋለች።
አሜሪካ ጥቃቱን ባደረሱ አካላት ላይ ምላሽ እንደምስጥ መዛቷ ይታወሳል።
እስራኤል እና የፍልስጤሙ ሀማስ ወደ ጦርነት ከገቡበት በፈረንጆቹ ከባለፈው አመት ጥቅምት ወር ጀምሮ 'አክሲስ ኦፍ ሪዚስታንስ' በመባል የሚታወቁት በኢራን የሚደገፉት ታጣቂ ቡድኖች በሊባኖስ፣ በየመን፣ በኢራቅ እና በሶሪያ እስራኤልን እና አሜሪካን ኢላማ ያደረጉ ጥቃቶችን አድርሰዋል።
ካታይብ ሂዝቦላ በኢራቅ በሚካሄዱ እስላማዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ ጠንካራ የሚባል የሻይት ታጣቂ ቡድን ነው። ይህ ቡድን የጋዛው ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ በኢራቅ እና በሶሪያ በሚገኙ የአሜሪካ ኃይሎች ላይ ለደረሱ 150 ጥቃቶች ኃላፊነቱን ወስዷል።
አሜሪካ ለደረሱባት ጥቃቶች የምትሰጣቸው ከባድ የአጸፋ ምላሾች፣ ወደ መረጋጋት እመጣች ያለችውን ኢራቅ ወደ አለመረጋጋት ውስጥ ይከታታል የሚል ስጋት በኢራቅ ባለስልጣናት ዘንድ ተፈጥሯል።
ቡድኑ ጥቃት ለማቆም የወሰነው የኢራቅ መንግስት ጉዳዩ እንዳይባባስ ባደረገው የቀናት ጥረት ነው ተብሏል።