የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ አጋር የሆነው የሊባኖሱ ሄዝቦላ በሰሜን እስራኤል በኩል ጦርነት ከፍቷል።
ሄዝቦላ ምን አይነት መሳሪያዎች ታጥቋል ?
የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ አጋር የሆነው የሊባኖሱ ሄዝቦላ በሰሜን እስራኤል በኩል ጦርነት ከፍቷል።
ከጥቅምት መጀመሪያ ጀምሮ በእስራኤል እና ሄዝቦለ መካከል እየተካሄደ ያለው የተኩስ ልውውጥ ከፈረንጆቹ 2006 ወዲህ ከፍተኛው መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል።
ሄዝቦላ በኢራን ድጋፍ ይደረግላቸዋል ከሚባሉት ታጣቂ ቡድኖች ጠንካራው መሆኑ ይነገራል። የሄዝቦላህ መሪ ሰይድ ሀሰን እንደሚሉት ከሆነ ቡድኑ 100ሺ የሚሆኑ ታጣቂዎች አሉት።
ሄዝቦላ የታጠቃቸው ሮኬቶች
የሄዝቦላ ወታደራዊ ጥንካሪ የተገነባው ባሉት በርካታ የርኬት ተተኳሾች ነው። ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ከሆነ ይህ የሻይት እስላማዊ ቡድን 100ሺ ሮኬቶችን ታጥቋል።
ሄዝቦላ ሙሉ እስራኤልን ሊመታ የሚችል ሮኬት መታጠቁን ተናግሯል።
ቡድኑ በፈረንጆቹ 2016 ከመሬት በ16ኪሎ ሜትር ላይ ርቃ የምትገኝን የእስራኤል መርከብ መትቶ በማውደም እና አራት ፐርሶኔሎችን በመግደል ጸረ-መርከብ ሚሳይል እንዳለው አረጋግጧል።
ድሮኖች/ሰው አልባ አውሮፕላኖች
ሄዝቦላ በራሱ የሰራቸውን አዩብ እና መርሳድ የተባሉ ሞዴሎችን ጨምሮ አነስተኛ ክብደት የሚሸከሙ ድሮኖች እንዳሉት ገልጿል።
ወታደራዊ ባለሙያዎች እንደሚናገሩት ከሆነ በርካሽ እና በከፍተኛ መጠን የሚመረቱት ድሮኖች በእስራኤሉ 'አይረን ዶም' ሚሳይል መከላከያ ስርአት ላይ ጫና የመፍጠር አላማ አላቸው።
እስራኤል፣ ኢራንን ሄዝቦላን በማስታጠቅ በተደጋጋሚ ከሳለች።
የሄዝቦላው መሪ በቅርቡ የፍልስጤም ታጣቂ ቡድን ከሆኑት ከሀማስ እና ከእስላማዊ ጁሃድ መሪዎች ጋር ተገናኝተው እስራኤልን ድል በሚያደርጉበት ጉዳይ ላይ መምከራቸውን መግለጻቸው ይታወሳል።
እስራኤል በጋዛ ውስጥ እያካሄደች ያለውን ዘመቻ አጠናክራ ቀጥላለች።