ሄዝቦላ ለሟቹ መሪው ነስረላህ የቀብር ስነስርዓት የሚያደርግበትን ቀን ይፋ አደረገ
የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላ መሪ የሟቹ መሪ ሀሰን ነስረላህ የቀብር ስነስርዓት በየካቲት 23፣2025 እንደሚፈጸም በትናንትናው እለት ይፋ አድርጓል።
የሄዝቦላ ዋና ጸኃፊ በመሆን ለ30 አመታት ያገለገለው ነስረላህ የተገደለው እስራኤል ባላፈው በመስከረም ወር በፈጸመችው መጠነሰፊ የአየር ጥቃት ነበር የተገደለው
ሄዝቦላ ለሟቹ መሪው ነስረላህ የቀብር ስነስርዓት የሚያደርግበትን ቀን ይፋ አደረገ።
የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላ መሪ የሟቹ መሪ ሀሰን ነስረላህ የቀብር ስነስርዓት በየካቲት 23፣2025 እንደሚፈጸም በትናንትናው እለት ይፋ አድርጓል።
የሄዝቦላ ዋና ጸኃፊ በመሆን ለ30 አመታት ያገለገለው ነስረላህ የተገደለው እስራኤል ባላፈው በመስከረም ወር በፈጸመችው መጠነሰፊ የአየር ጥቃት ነበር የተገደለው። እስራኤል ግድያውን ከፈጸመች በኋላ የሊባኖስን ድንበር በሟቋረጥ በእግረኛ ጦር ዘመቻ መክፈቷ ይታወሳል።
በነስረላህ የተተካው መሪ ናይም ቃሲም በቴሌቪዥን ባስተላለፈው መልእክት ነስረላህ የተገደለው "በአስቸጋሪ ሁኔታ ወቅት" በመሆኑ በሀይማኖታዊ ስነስርአት መሰረት ቡድኑ ጊዜያዊ ቀብር ለማድረግ መገደዱን ተናግሯል።
ቃሲም እንደገለጸው አሁን ላይ ቡድኑ ለነስረላህ እና ነስረላህ ከተገደለ ከአንድ ሳምንት ገደማ በኋላ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት ለተገደለው ከፍተኛ የሄዝቦላ ባለስልጣን ሀሽም ሰይፈዲን ብዙ ህዝብ የሚሳተፍበት የቀብር ስነስርአት ለማድረግ ወስኗል።
ቃሲም ሰይፈዲን የነስረላህ ምትክ ሆኖ መሾሙን እና ይፋ ከመሆኑ በፊት መገደሉን ለመጀመሪያ ጊዜ አረጋግጧል። ሰይፈዲንም በዋና ጸኃፊ ማዕረግ የቀብር ስነስርአቱ ይፈጸማል ብሏል ቃሲም።
የነስረላህ እና ሰይፈዲን እንዲሁም የሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ግድያ ሄዝቦላ ኪሳራ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። ቡድኑ ጥቅምት 29፣2024 የቡድኑ ምክትል መሪ የነበረው ቃሲምን መሪ ሆኖ መመረጡን ይፋ አድርጓል።
በህዳር መጨረሻ በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት በሄዝቦላ እና እስራኤል መካከል የነበረው ግጭት ቆሟል።እስራኤል በ60 ቀናት ውስጥ ከደቡብ ሊባኖስ እንድትወጣ እና ሄዝቦላ ደግሞ ተዋጊዎቹንና መሳሪያውን ከቦታው እንዲያስወጣና በምትኩ የሊባኖስ ጦር ቦታውን እንዲይዝ ስምምነቱ ያስገድዳል።
ቀነገደቡ ባለፈው ወር እስከ የካቲት 18፣2025 ድረስ ተራዝሟል። ሄዝቦላ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሷል የምትለው እስራኤል በተወሰኑ የሊባኖስ ክፍሎች የአየር ጥቃት መፈጸሟን ቀጥላለች።
ነገርግን ሄዝቦላ ለተኩስ አቁሙ መጣስ እስራኤልን ተጠያቂ ያደርጋል።