እስራኤል የጋዛ አል-ሺፋ ሆስፒታልን አልመታሁም ስትል አስተባብላለች
ሃማስ በእስራኤል ላይ ድንገተኛ እና ያለተጠበቀ ጥቃት መሰንዘሩን ተከትሎ የተቀሰቀሰው ጦርነት ከተጀመረ 36ኛ ቀኑን አስቆጥሯል።
እስራኤልም ራሷን ለመከላከልና የአጸፋ እርምጅ ለመውሰድ ጋዛ ላይ ድብደባ ከጀመረች 36 ቀናት የተቆጠሩ ሲሆን፤ በእስራኤል ጦርና በሃማስ ታጣቂዎች መካከል የተቀከቀሰው ጦርነትን እንደቀጠለ ይገኛል።
እስራኤል ጦር አዳሩን በጋዛ ላይ የማያባራ የአየር ድብደባ ሲያደረግ ያደረ ሲሆን፤ በጋዛ የሚገኘውን ግዙፉን አል-ሺፋ ሆስፒታልን መምታቷ ተነግሯል።
የእስራኤል ጦር በበኩሉ አል-ሺፋ ሆስፒታልን አልመታሁም ሲለ ያስተባበለ ሲሆን፤ በሆስፒታሉ ዙሪያ ከሃማስ ታጣቂዎች ጋር እየተዋጋ መሆኑን አስታውቋል።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስቴር የሊባኖሱን ሄዝቦላህ ያስጠነቀቀ ሲሆን፤ በጋዛ እያደረገ ያለውን በቤሩት ሊደግም እንደሚችልም ዝቷል።
የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮአቭ ጋላንት፤ በኢራን የሚደገፈው ሄዝቦላህ ሊባኖስን ወደ ጦርነት ሊያስገባ ነው ሲሉ አሳስበዋል።
ጦርነቱ ያስከተለው ሰብዓዊ ቀውስ
በእስራኤል የአየር ድብደባ የተገደሉ ፍሊስጤማውያን ቁጥር 10 ሺህ ገደማ ከየደረሰ ሲሆን፤ እነዚህም ከ4 ሺህ 500 በላይ ህጻናት መሆናቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በጋዛ የተገደሉ የሰባዓዊ ሰራተኞቹ ቁጥር ከ100 ማለፉን እና ይህም በታሪክ በአንድ ገጭት ላይ የተገደሉ ከፍተኛ የሰራተኞቹ ቁጥር መሆኑን አስታውቋል።
በእስራኤል በሃማስ ጥቃት የሞቱ ሰዎች ቁጥርን 1 ሺህ 400 ወደ 1 ሺህ 200 ዝቅ አድርጋለች። ከ240 በላይ ሰዎች ገድሞ በሃማስ እንደታገቱ ይገኛሉ።