ሀሰን ናስራላህን በእርግጠኝነት ይተካሉ የተባሉት ሀሽም ሳፊዲን እንዴት ተገደሉ?
እስራኤል ሒዝቦላህ ተተኪ እስከሚያጣ ድረስ እየተከታተለች በመግደል ላይ ነች
ሒዝቦላህ እና ሐማስ የእስራኤል የምንግዜም ጠላት ናቸው በሚል የአየር እና ምድር ላይ ድብደባው እንደቀጠለ ነው
ሀሰን ናስራላህን በእርግጠኝነት ይተካሉ የተባሉት ሀሽም ሳፊዲን እንዴት ተገደሉ?
የፍልስጤሙ ሐማስ ከአንድ ዓመት በፊት በእስራኤል ላይ ያልተጠበቀ ጥቃት መክፈቱን ተከትሎ በመካከለኛው ምስራቅ የተጀመረው ጦርነት መቋጫ አላገኘም።
አድማሱን እያሰፋ የመጣው ይህ ጦርነት የእስራኤል ጦር ከጋዛ ባለፈ ወደ ሊባኖስ በመግባት ከሂዝቦላህ ተዋጊዎች ጋር እየተዋጉ ናቸው።
ሐማስ እና ሂዝቦላህ በእስራኤል ታሪካዊ ጠላት ናቸው በሚል የቡድኖቹን አመራሮች በተለያዩ መንገዶች ታድነው እየተገደሉ ናቸው።
መስከረም ወር ላይ ሂዝቦላህን ላለፉት 30 ዓመታት የመሩት ሀሰን ናስራላህ በቤሩት አስቸኳይ ስብሰባ እያደረጉ እያሉ መገደላቸው ይታወሳል።
እስራኤል ይህን ጥቃት አሜሪካ ሰራሽ የሆነው "በንከር" የተሰኘውን ልዩ ቦምብ የተጠቀመች ሲሆን በዚህ ወቅት ሀሰን ናስራላህ እና ሌሎች የቡድኑ አመራሮችም አብረው ተገድለዋል።
ይህን ተከትሎ ሂዝቦላህን በቀጣይ ማን ሊመራው ይችላል? በሚል ለቀረበው ጥያቄ አጎታቸው ናቸው የተባሉት ሀሽም ሳፊዲን የብዙዎች ግምት ነበሩ።
ይሁንና እኝህ ሰው ከዛሬ ነገ የሂዝቦላህ መሪ መሆናቸው በይፋ ይታወጃል ቢባልም ሳይሆን ቀርቷል።
ሀሽም ሳፊዲን ሀሰን ናስራላህ በተገደሉ ዕለት ከምድር በታች በተሰራ የሂዝቦላህ ቢሮ ውስጥ ነበሩ ተብሏል።
ያሉበት ህንጻ በከባድ ቦምብ መደብደቡን ተከትሎ ከምድር በታች የነበሩት ሀሽም ሳፊዲን አየር አጥሯቸው ህይወታቸው አልፎ መገኘታቸውን የሊባኖስ ቴሌቪዥን ዘግቧል።
ሀሽም ሳፊዲን ሂዝቦላህ በእስራኤል ላይ ከሚወሰዱ ማናቸውን ጥቃቶች ጀርባ የነበሩ ዋና አስፈጻሚ እንደነበሩም ተገልጿል።