ሄዝቦላህ በእስራኤል የቅኝት ጣቢያ ላይ መጠነሰፊ የሮኬት ጥቃት መፈጸሙን አስታወቀ
አሁን ያለው የእስራኤል እና የሄዝቦላ ግጭት መባባስ በፈረንጆቹ 2006 በሁለቱ መካከል የነበረውን ከባድ ግጭት የሚያስታውሰ ነው ተብሏል
ሄዝቦላ ይህን ጥቃት የሰነዘረው የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ግዛት ውስጥ ገብቶ ለፈጸመው ከባድ ጥቃት ምላሽ ነው ተብሏል
የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላ በዛሬው በእስራኤል የአየር ቅኝት ጣቢያ ላይ በመጠነሰፊ የሮኬት ጥቃት መሰንዘሩን አስታውቋል።
ሄዝቦላ ይህን ጥቃት የሰነዘረው የእስራኤል ጦር በሊባኖስ ግዛት ውስጥ ገብቶ ለፈጸመው ከባድ ጥቃት ምላሽ ነው።
እስራኤል እና በኢራን ይደገፋል የሚባለው ሄዝቦላ ባለፈው ጥቅምት ወር ግጭት ውስጥ ከገቡ ወዲህ የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች በሌባኖስ ውስጥ ርቀው በመብረር ቤካ በተባለው ሸለቆ ባደረጉት ድብደባ ሁለት የሄዝቦላ ታጣቂዎች መግደላቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።
የእስራኤል ጦር በቦታው ላይ ያለውን የሄዝቦላ የአየር መከላከያ የመታው ቀደም ሲል በሄዝቦላ ተመቶ ለወደቀው የእስራኤል ድሮን ምላሽ ነው ብሏል።
ሄዝቦላ ደግሞ በቤካ የደረሰውን ጥቃት ለመበቀል እስራኤል በወረራ በያዘችው ጎላን ሀይት ውስጥ በሚገኘው የእስራኤል የጦር ሰፈር ላይ በትናንትናው 60 ሮኬቶችን ማስወንጨፉን አስታውቋል።
ቡድኑ በዛሬው እለት ጠዋት ምን ያህል ሮኬቶች እንዳስወነጨፈ ቁጥሩን ግልጽ ባያደርግም ብዙ መሆኑን ግን ጠቅሷል።
አሁን ያለው የእስራኤል እና የሄዝቦላ ግጭት መባባስ በፈረንጆቹ 2006 በሁለቱ መካከል የነበረውን ከባድ ግጭት የሚያስታውሰ ነው ተብሏል።
ሄዝቦላ ከእስራኤል ጋር እየተዋጋ ላለው የፍልስጤሙ ታጣቂ ቡድን ሀማስ አጋርነቱን አሳይቷል።