የሄዝቦላ የቀድሞ መሪ ሀሰን ነስረላህ የቀብር ስነስርዓት ተፈጸመ
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሊባኖሳውያን በቤሩት ተሰባስበው ለሀሰን ነስረላህ አስከሬን ሽኝት አድርገዋል

የሄዝቦላ ዋና ጸኃፊ በመሆን ለ30 አመታት ያገለገለው ነስረላህ በመስከረም ወር በእስራኤ የአየር ጥቃት ነበር የተገደለው
የሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላ የቀድሞ መሪ ሀሰን ነስረላህ የቀብር ስነስርዓት በዛሬው እለት በአስር ሺቸ የሚቆጠሩ ሊባሳውያን በተገኙበት ተፈጽሟል።
በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሊባሳውያንም በቤሩት በተካሄደው የሽኝት እና የቀብር ስነ ስርዓት ላይ በመታም የሄዝቦላ የቀድሞ መሪ ሀሰን ነስረላህን አስከሬን ተሰናብተዋል።
የናስራላህ ፎቶዎችን እና የሄዝቦላህ ባንዲራዎችን የያዙ ከሊባኖስ እና ከሌሎች የአከባቢው ሀገራት የመጡ ደጋፊዎች 55 ሺህ መቀመጫ ያለውን ካሚል ቻሙን ስፖርት ሲቲ ስታዲየም በመሙላት ሽኝቱን ታድመዋል ነው የተባለው።
የሄዝቦላ ዋና ጸኃፊ በመሆን ለ30 አመታት ያገለገለው ነስረላህ የተገደለው እስራኤል ባላፈው በመስከረም ወር በፈጸመችው መጠነሰፊ የአየር ጥቃት ነበር የተገደለው።
እስራኤል ግድያውን ከፈጸመች በኋላ የሊባኖስን ድንበር በሟቋረጥ በእግረኛ ጦር ዘመቻ መክፈቷ ይታወሳል።
የነስረላህ እና ሰይፈዲን እንዲሁም የሌሎች ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዦች ግድያ ሄዝቦላ ኪሳራ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል።
ቡድኑ ጥቅምት 29፣2024 የቡድኑ ምክትል መሪ የነበረው ቃሲምን መሪ ሆኖ መመረጡን ይፋ አድርጓል።
በህዳር መጨረሻ በተደረሰው የተኩስ አቁም ስምምነት በሄዝቦላ እና እስራኤል መካከል የነበረው ግጭት ቆሟል።
እስራኤል በ60 ቀናት ውስጥ ከደቡብ ሊባኖስ እንድትወጣ እና ሄዝቦላ ደግሞ ተዋጊዎቹንና መሳሪያውን ከቦታው እንዲያስወጣና በምትኩ የሊባኖስ ጦር ቦታውን እንዲይዝ ስምምነቱ ያስገድዳል።
ቀነገደቡ ባለፈው ወር እስከ የካቲት 18፣2025 ድረስ ተራዝሟል። ሄዝቦላ የተኩስ አቁም ስምምነቱን ጥሷል የምትለው እስራኤል በተወሰኑ የሊባኖስ ክፍሎች የአየር ጥቃት መፈጸሟን ቀጥላለች።
ነገርግን ሄዝቦላ ለተኩስ አቁሙ መጣስ እስራኤልን ተጠያቂ ያደርጋል።