ከሀሰን ነስረላህ ጋር የተገደሉ የሄዝቦላህ ቁልፍ መሪዎች እነማን ናቸው?
በእስራኤል የአየር ድብደባ ከሀሰን ነስረላህ ጋር 20 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል
የእስራኤል ጦር ከሀሰን ነስረላህ ጋር የተገደሉ የሄዝቦላህ መሪዎች ስም ይፋ አድርጓል
የእስራኤል ጦር ከሄዝቦላህ መሪ ሀሰን ነስረላህ ጋር የተገደሉ ቁልፍ የቡድኑ መሪዎችን ማንነት በዛሬው እለት ይፋ እድርጓል።
የእስራኤል ጦር ዛሬ ይፋ ባደረገው እና አል አይን ኒውስ በተመለከተው መግለጫ ላይ፤ በቤሩት ደቡባዊ ክፍል በሚገኘው የሄዘቦላህ ዋና መስሪያ ቤት በፈጸመ ጥቃት ከሀሰን ነስረላህ በተጨማሪ 20 የቡድኑ መሪዎች መገደላቸውን አስታውቋል
በአርብ እለቱ የአየር ድብደባ የከሄዝቦላህ መሪው ሀሰን ነስረላህ በተጨማሪ የሄዝቦላህ ቁልፍ ሰው የነበሩት ደቡብ እዝ ዋና አዛዥ አሊ ካርኪን መገደሉም የእስራኤል ጦር በመግለጫው አመላክቷል።
የቡድኑ ቅልፍ ሰዉ ከሆኑት ሀሰን ነስራላህ እና አሊ ካርኪ በተጨማሪም በተለያየ የአመራነት ደረጃ ላይ የሚገኙ 20 የሄዝቦላህ አመራሮችን መግደሉን ነው የእስራኤል ጦር የገለጸው።
በእስራኤ ከተገደሉ የሄዝቦላህ ቅልፍ ሰዎች የተወሰኑት…
-ኢብራሂም ሁሴን ጃዝኒ- የሀሰን ነስረላህ የግል ጥበቃ ቡድን መሪ
-ሰሚር ቶፊክ- ለበሽብር ጉዳይ ረጅም ዓመታት የሀሰን ነስረላህ አማራሪ
-አብዱል አሚር መሃመድ ሳበሊኒ- የሄዝቦላ የኃይል ግንባታ ከፍተኛ አመራር
-አሊ ናይፍ አዩብ- የሄዝቦላህ ለክፈኛ የተኩስ ቁጥጥር ኃላፊ ናቸው።
የእስራኤል ጦር በአርብ ምሽት በቤሩት በፈጸመው የአየር ጥቃት የሄዝቦላን ዋና ጸኃፊ ሀሰን ነስረላህን መግደሉን ማስታወቁን ይታወሳል።
የሊብኖሱ ሄዝቦላህ መሪው ሼክ ሀሰን ናስራላህ መገደላቸውን በትናንትናው እለት ባወጣው መግለጫ ያረጋገጠ ሲሆን፤ ቀብሩ መች እና የት ይፈጸማል የሚለውን ከመግለጽ ተቆጥቧል።