ሂዝቦላህ በሰሜናዊ እስራኤል የ14 መኖሪያ መንደር ነዋሪዎች ቤታቸውን እንዲለቁ አስጠነቀቀ
የእስራኤል ጦር የእስራኤል ጦር ከህዝብ መኖሪያ ቤት አቅራቢያ መስፈሩን ገልጿል
የእስራኤል-ሒዝቦላህ ጦርነት ከተጀመረ አንድ ወር አልፎታል
ሂዝቦላህ በሰሜናዊ እስራኤል የ14 መኖሪያ መንደር ነዋሪዎች ቤታቸውን እንዲለቁ አስጠነቀቀ
ከአንድ ዓመት በፊት የፍልስጤሙ ሐማስ በእስራኤል ላይ ልተጠበቀ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የተጀመረው ጦርነት አድማሱን እያሰፋ ይገኛል፡፡
ከአንድ ወር በፊት በሊባኖሱ ሂዝቦላህ እና እስራኤል ጦር መካከል ይፋዊ ጦርነት የተጀመረ ሲሆን የእስራኤል ጦር ወደ ደቡባዊ ሊባኖስ ገብቶ ከሂዝቦላህ ተዋጊዎች ጋር እየተዋጋ ይገኛል፡፡
በሁለቱ ድንበር አቅራቢያ የነበሩ ዜጎች መኖሪያ ቤታቸውን እየለቀቁ ሲሆን በሰሜናዊ እስራኤል 14 መኖሪያ መንደሮች ነዋሪዎች ቤታቸውን ለቀው እንዲሄዱ ሂዝቦላህ አስጠንቅቋል፡፡
ሂዝቦላህ በሰሜናዊ እስራኤል የሚኖሩ እስራኤላዊያን መኖሪያ ቤታቸውን እንዲለቁ ያስጠነቀቀው የሀገሪቱ ጦር ነዋሪዎች ባሉባቸው አካባቢዎች ሰፍሯል በሚል ነው፡፡
ነዋሪዎች ማስጠንቀቂያ ችላ ብለው ለሚደርስባቸው ጥቃት ሀላፊነቱን እንደማይወስድም ሂዝቦላህ አስታውቋል፡፡
እስራኤል ሂዝቦላህ እና ሐማስን ጨምሮ በመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት ውስጥ ያሉ ጸረ እስራኤል ድርጅቶች በእስራኤል የሚደገፉ ናቸው ስትል ትከሳለች፡፡
የየመኑ የሁቲ አማጺ ቡድን በኢራን ይደገፋሉ ተብለው ከተለዩ ድርጅቶች መካከል አንዱ ሲሆን በቀይ ባህር ከእስራኤል ጋር ግኝኑነት አላቸው የተባሉ መርከቦችን እየመታ ይገኛል፡፡
እስራኤል በየመኑ ሁቲ አማጹ ቡድን ይዞታዎች ላይ የአየር ድብደባ ያደረገች ሲሆን አሜሪካም የምድር ቦምቦችን በመጠቀም በቡድኑ ላይ ተደጋጋሚ የአየር ላይ ጥቃት ሰንዝራለች፡፡
በኢራን ይደገፋሉ ከሚባሉት ውስጥ እስራኤል ከሐማስን እና ሂዝቦላህ ጋር ፋዊ ጦርነት ውስጥ ስትሆን የቡድኖቹን አመራሮችም ገድላለች፡፡