ኢራን በበኩሏ ራሴን የመከላከል መብት አለኝ ከማለት ውጪ የአጸፋ እርምጃ ስለመውሰዷ እስካሁን አልተናገረችም
አሜሪካ ኢራን በእስራኤል ላይ የአጸፋ እርምጃ እንዳትወስድ አስጠነቀቀች፡፡
ከአንድ ዓመት በፊት የፍልስጤሙ ሐማስ በእስራኤል ላይ ልተጠበቀ ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ የተጀመረው ጦርነት አድማሱን እያሰፋ ይገኛል፡፡
እስራኤል በኢራን ይደገፋሉ የምትላቸው የሐማስን እና የሊባኖሱን የሂዝቦላህ መሪዎችን ገድላለች፡፡
ኢራን ለእስራኤል ጥቃት በያዝነው ወር መግቢያ ላይ በእስራኤል ላይ የሚሳኤል ጥቃት የፈጸመች ሲሆን በትናንትናው ዕለት ደግሞ እስራኤል በኢራን ጥቃት የአጸፋ እርምጃ ወስዳለች፡፡
ይህን ተከትሎ ሁለቱ ሀገራት ወደ ፊት ለፊት ጦርነት እንዳይገቡ የተሰጋ ሲሆን አሜሪካ ኢራን ለእስራኤል የአጸፋ እርምጃ እንዳትወስድ አስጠንቅቃለች፡፡
በ6 ከተሞች በ20 ኢላማዎች ላይ ያነጣጠረው የእስራኤል ጥቃት
የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስትር ሊዮልድ ኦስቲን እንዳሉት የመካከለኛው ምስራቅ ወደ ተባባሰ ጦርነት እንዳይገባ ሁለቱም ሀገራት የገቡበትን መካረር እንዲያረግቡ ጥሪ ማቅረባቸውን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጉዳዩ ላይ ባወጣው መግለጫ፤ የእስራኤልን የአየር ድብደባ በማውገዝ፤ ኢራን ራሷን የመከላከል መብት እና ግዴታ አለባት ሲል አስታውቋል።
የኢራን ጦር በበኩሉ፤ እስራኤል በኢላም እና ኩዜስታን ግዛቶች ድንብር አቅራቢያ ላይ የሚገኙ የኢራን ራዳር ስርዓት ላይ ቀለል ያሉ ሚሳዔሎችን ተጠቅመው ጥቃት መሰንዘራቸወን አስታውቋል።
ይህ በዚህ እንዳለ ግን ኢራን ለእስራኤል ጥቃት የአጸፋ እርምጃ ስለመውሰዷ እስካሁን ያለችው ነገር የሌለ ሲሆን ለአሜሪካም ማስጠንቀቂያ እስካሁን ምላሽ አልሰጠችም፡፡