10 ሙስና የተንሰራፋባቸው ሀገራት
በትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የ2023 ሪፖርት ሶማሊያ ቀዳሚዋ ሙስና የተስፋፋባት ሀገር ሆናለች
ኢትዮጵያ ደግሞ በ37 ነጥብ 98ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጣለች
ትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የ180 ሀገራትን የሙስና ተጋላጭነት በማጥናት ደረጃቸውን ይፋ አድርጓል።
23 ሀገራት በ2022 ከነበራቸው ደረጃ ዝቅ ብለዋል ያለው የተቋሙ ሪፖርት፥ ከ2016 ጀምሮ የህግ የበላይነት መከበርና ፍትህ የማስፈን ጥረት እየተዳከመ መሄዱን ጠቁሟል።
ዴንማርክ ከ100 ነጥብ 90 በማግኘት ለስድስተኛ ተከታታይ አመት ዝቅተኛ ወይንም ምንም ሙስና የማይታይባት ሀገር ሆናለች። ፊንላንድ እና ኒውዝላንድ ደግሞ በ87 እና 85 ነጥብ ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።
ኖርዌይ፣ ሲንጋፖር፣ ስዊድን፣ ስዊዘርላንድ፣ ኔዘርላንድስ፣ ጀርመን እና ሉግዘንበርግ እስከ 10ኛ ያለውን ደረጃ መያዛቸውንም የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽናል የ2023 ሪፖርት ያመላክታል።
ካለፈው አመት በአንድ ነጥብ ዝቅ ያለችው ኢትዮጵያም በ37 ነጥብ 98ኛ ደረጃን ይዛለች።
ሶማሊያ በ2023ም ሙስና የተንሰራፋባት ሀገር በመሆን በ11 ነጥብ የመጨረሻውን ደረጃ (180ኛ) ይዛለች።
በ2023 ሙስና የተንሰራፋባቸው 10 ሀገራት የትኞቹ ናቸው? በቀጣዩ ምስል ይመልከቱ፦