የስፔኑ የግል ወታደራዊ ኩባንያ በ3 ሺህ 400 የሮ ወርሃዊ ደመወዝ ተዋጊዎችን እየመለመለ ነው
ኩባንያው ወታደሮችን የሚመለምለው ወደ ዩክሬን ለመላክ እንደሆነ ገልጿል
ተዋጊዎቹ በህይወት የመመለስ እድላቸው እጅግ የመነመነ ነው ተብሏል
የስፔኑ የግል ወታደራዊ ኩባንያ በ3 ሺህ 400 ዩሮ ወርሃዊ ደመወዝ ተዋጊዎችን እየመለመለ ነው፡፡
የሩሲያው ወታደራዊ ቅጥረኛ ተዋጊ ቡድን አቻ የሆነ ተቋም በስፔን መመስረቱን ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
እንደዘገባው ከሆነ የስፔን የግል ወታደራዊ ቡድን ለዩክሬን ተዋጊዎችን በመመልመል ላይ መሆኑን አስታውቋል፡፡
ፈቃደኛ ሆነው ወደ ዩክሬን የውጊያ ግንባሮች ለማምራት ፈቃደኛ የሆኑ ሰዎች ስልጠናውን ከወሰዱ በኋላ በ3 ሺህ 400 ዩሮ ወርሃዊ ደመወዝ ከዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር ጋር ውል ይዋዋላሉ ተብሏል፡፡
ፑቲን የዩክሬንን ጦርነት እየመሩ ካሉ ጀነራሎች ጋር መከሩ
ስልጠናው ከባድ ነው የተባለ ሲሆን በስልጠና ወቅት ሁለት ሌሊት እና ሶስት ቀናትን ያለ እንቅልፍ ማሳለፍ ከሰልጣኞች እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል፡፡
ኩባንያው በውትድርና ሙያ ሁለት ዓመት እና ከዚያ በላይ ልምድ ያላቸው ሰዎችን ሁሉ በመመልመል ላይ ሲሆን ወደ ዩክሬን ያመሩ ተዋጊዎች በህይወት የመመለስ እድላቸው አነስተኛ ይሆናል ተብሏል፡፡
ይህ ስሙ ያልተጠቀሰው የግል ወታደራዊ ኩባንያ ከዩክሬን በተጨማሪ በሌሎች ሀገራትም ተዋጊዎችን እንደሚልክ ተገልጿል፡፡
የሩሲያ ዩክሬን ጦርነት ከተጀመረ 18 ወራት ያለፈው ሲሆን ዩክሬን ጦርነቱ ከመጀመሩ በፊት 500 ሺህ ወታደሮች እንደነበሯት የስታስቲካ መረጃ ያስረዳል፡፡
እስካሁን ባለው ጦርነት 200 ሺህ ገደማ ያህሉ የዩክሬን ወታደሮች የተገደሉ ሲሆን የተዋጊዎቿን ብዛት በማስፋት ላይ እንደሆነች ተገልጿል፡፡