በአሜሪካ ከሚኖሩ አፍሪካዊያን ውስጥ የኢትዮጵያዊያኑ ተወዳዳሪነት ምን ይመስላል? ዓመታዊ ገቢያቸውስ ምን ያህል ነው?
በአሜሪካ ከሚኖሩ አፍሪካዊያን ስደተኞች ውስጥ ከፍተኛ ገቢ የሚያገኙት እነማን ናቸው?
ከ4 ሚሊዮን በላይ አፍሪካዊያን ስደተኞች በአሜሪካ ይኖራሉ
በአሜሪካ ከሚኖሩ አፍሪካዊያን ውስጥ የኢትዮጵያዊያኑ ተወዳዳሪነት ምን ይመስላል?
የዓለማችን ቁጥር አንድ ሀያል ሀገር በሆነችው አሜሪካ ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የበርካታ ሀገራት ስደተኞች ይኖራሉ።
ከ4 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ አፍሪካዊያን ስደተኞችን ያስጠለለችው አሜሪካ ኢኮኖሚዋን ከኢትዮጵያ እና ከሌሎች ሀገራት በሚመጡ ስደተኞች ትደጉማለች።
በአሜሪካ ከሚኖሩ አፍሪካዊያን ስደተኞች ውስጥ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት አብዛኛውን ድርሻ እንደሚይዙ የሀገሪቱ ስነ ህዝብ ኢንስቲትዩት ሪፖርት ያስረዳል።
ቢዝነስ ኢንሳይደር አፍሪካ የዚህን ተቋም ሪፖርት ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ከሆነ የአሜሪካዊያን ስደተኞች ግን ዓመታዊ አማካኝ ገቢ 77 ሺህ ዶላር ሲሆን አፍሪካዊያን ግን በዓመት ከ77 ሺህ ዶላር በላይ ገቢ ያገኛሉ።
እንደ ሪፖርቱ ከሆነ ደቡብ አፍሪካዊያን ስደተኞች በዓመት 108 ሺህ ዶላር ገቢ በማግኘት ቀዳሚ ሆነዋል።
ጎረቤት ሀገር ኬንያዊያን ስደተኞች ደግሞ በዓመት 97 ሺህ ዶላር ገቢ ሲያገኙ ካሜሩናዊያን ደግሞ በ90 ሺህ ዶላር ሁለተኛ እና ሶስተኛ ናቸው።
የግብጽ፣ ጋና እና ናይጀሪያ ስደተኞች ደግሞ እንደ ቅደም ተከተላቸው ከ4ኛ እስከ6ኛ ያለውን ደረጃ ሲይዙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ደግሞ በዓመት 72 ሺህ ዶላር ገቢ እንደሚያገኙ ተገልጿል።
ይህ በዚህ እንዳለ ጃማይካዊያን፣ ሀይቲ፣ ናይጀሪያ፣ ጋና እና ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ደግሞ በአሜሪካ ከተጠለሉ ጥቁሮች መካከል በቁጥር ብልጫ አላቸው ተብሏል
ኢትዮጵያዊያኑን ጨምሮ አብዛኞቹ የአፍሪካ ስደተኞች ወደ አሜሪካ የተሰደዱት በሀገራቸው ባሉ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ የተሻለ ደህንነት በመፈለግ እና በድህነት ምክንያት የተሰደዱ ናቸው ተብሏል።