የታሪክ ተመራማሪዎች ከ51 አመት በፊት በሙኒክ ኦሎምፒክ የደረሰውን ጥቃት ሊመረምሩ ነው
ተመራማሪዎቹ ምርመራውን የሚያካሄዱት በሶስት አመታት ጊዜ ውስጥ መሆኑን አሶሼትድ ኘሬስ ዘግቧል
ጀመርን በጥቃቱ ወቅት የፈጸመችውን ስህተት አምና የምርመራ ቡድን እንዲቋቋም አድርጋለች
የታሪክ ተመራማሪዎች በፊረንጆቹ 1972 በሙኒክ ኦሎምፒክ የደረሰውን ጥቃት ለመመርመር ስራ መጀመራቸው ተገለጸ።
ተመራማሪዎቹ ምርመራውን የሚያካሄዱት በሶስት አመታት ጊዜ ውስጥ መሆኑን አሶሼትድ ኘሬስ ዘግቧል።
የተመራማሪ ቡድኑ የመጀመሪያውን ሰብሰባ በዛሬው እለት በሀገር ውስጥ ሚኒስቴር ውስጥ አካሂዷል።
የሀገር ውስጥ ሚኒስትሯ ናንሲ ፌዘር "በዚህ ዘግናኝ ጥቃት ዙሪያ ያሉ በመጨረሻም በጥልቀትና በግልጸኝነት ይመረመራሉ" ሲሉ ቃል ገብተዋል።
ፌዘር እንደገጹት በምርመራው የሚገኘው ውጤት መልስ ላላገኙ በርካታ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ እና የጀርመን መንግስትም ለተጎጂ ቤተሰቦች እና ለህዝቡ መልስ እንዲሰጥ ያስችለዋል።
ሚኒስትሯ በምርምሪ ዙሪያ መደበኛ የሆነ የጹሁፍ መግለጫ እንደሚኖር ተናግረዋል።
ባለፈው መስከረም ውስጥ የጀርመን ፕሬዝደንት ፍራንክ ዋልተር ስቴንሜየር የእስራኤል አቻቸውን እና የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ አትሌቶችን ባገኙበት ወቅት ከጥቃቱ በፊት፣ በጥቃቱ ወቅት እና ከጥቃቱ በኋላ ጀርመን ላሳየችው ስህተት ይቅርታ ጠይቀዋል።
ፕሬዝደንቱ ይህን ያሉት የጥቃቱ 50ኛ አመት መታሰቢያ ዝግጅት ላይ ነው።
ከቀናት ቀደም ብሎ ለተጎጂ ቤተሰቦች 30 ሚሊዮን ዶላር ለመካስ ስምምነት ላይ ደርሷል።
ጀመርን በጥቃቱ ወቅት የፈጸመችውን ስህተት አምና የምርመራ ቡድን እንዲቋቋም አድርጋለች።
በመስከረም 1972፣ ጥቁር መስከሰም የሚባለው የፍልስጤም ቡድን ስምንት አባላት በኦሎምፒክ መንደር ላይ በመግባት ጥቃት አድርሰው ነበር።
በጥቃቱ የቦክስ አሰልጣኙን ሞሼ ዌይነበርግን እና የክብደት አንሽውን ዮሲ ሮማኖ ተገደሉ።
ጥቂት የእስራኤል አትሌቶች ሲያመልጡ ዘጠኙ ተይዘው ነበር። አጋቾቹ በእስራኤል የተያዙት 200 ፍልስጤማውያን እንዲለቀቁ ጥያቄ አቅርበው ነበር።
ከአንድ ቀን ድርድር በኋላ በተደረሰ ስምምነት የታገቱ እና አጋቾቹ ወደ ውጭ እንዲሄዱ ተደርጎ ነበር።