ጀርመን በሩሲያ ጉዳይ አፍሪካዊያንን ይቅርታ እንድትጠይቅ ያደረጋት ምክንያት ምንድን ነው?
የጀርመን ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር በትዊተር ገጹ አፍሪካዊያንን ዝቅ የሚያደርግ ይዘት ማሰራጨቱን ቁጣን አስተናግዷል
የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በትዊተር መልዕክቱ አፍሪካዊያንን እንዳስከፋ በመግለጽ ይቅርታ ጠይቋል
የጀርመን ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር በትናንትናው ዕለት በትዊተር ገጹ ያሰራጨው እንድ ይዘት ብዙ ውግዝቶችን አስከትሎበታል።
የሩሲያ ውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ወደ አፍሪካ ለይፋዊ ጉብኝት መምጣታቸውን ተከትሎ የጀርመን ውጪ ጉዳይ ሚንስቴር በትዊተር ገጹ ስለ ላቭርቭ ጉብኝት ስላቅ የሚመስል ይዘት አሰራጭቷል።
- የሩሲያው ከፍተኛ ዲፕሎማት እና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ያነሷቸው አንኳር ጉደዮች ምንድን ናቸው?
- የሩሲያው ከፍተኛ ዲፕሎማት ስለ “ደቡብ አፍሪካ-ሩሲያ የጋራ ወታደራዊ ልምምዶች” ምን አሉ ?
"የሩሲያ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር አፍሪካ ናቸው፣ ሰርጊ ላቭሮቭ ወደ አፍሪካ የተጓዙት ነብር ለመጎብኝት አይደለም፣ የሩሲያ ዩክሬን ወረራን ህጋዊ ለማድረግ እንጂ" የሚል መልዕክት በጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ትዊተር ገጽ ላይ ተሰራጭቷል።
ይህን ይዘት ተከትሎም በርካታ ጀርመናዊያን እና አፍሪካዊያን በጀርመን መንግሥት መበሳጨታቸውን የሚገልጹ ምላሾችን ሰጥተዋል።
የአፍሪካ ህብረት ለጀርመን በሰጠው ምላሽ አፍሪካ የዱር እንስሳት መገኛ ብቻ አለመሆኗን እና የሰዎችም መገኛ እንደሆነች በትዊተር ገጹ ምላሽ ሰጥቷል።
በጀርመን መንግሥት መልዕክት ማዘኑን የገለጸው አፍሪካ ህብረት የውጭ ግንኙነት ቀልድ ባለመሆኑ ጀርመን ከቅኝ ግዛት አስተሳሰቧ እንድትታቀብ ሲል አሳስቧል።
የጀርመን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር በትዊተር መልዕክቱ አፍሪካዊያንን እንዳስከፋ በመግለጽ ይቅርታ ጠይቋል።
ሚንስቴሩ አክሎም የሩሲያ ውጪ ጉዳይ ሚንስትር በዩክሬን እየፈጸሙት ያለውን ወንጀል ለመደበቅ ወደ አፍሪካ ተጉዘዋል ማለት እንደፈለገ በይቅርታ መልዕክቱ ላይ ጠቅሷል።
የሩሲያ ውጪ ጉዳይ ሚንስትር ሰርጊ ላቭሮቭ ደቡብ አፍሪካን፣ ኢስዋትኒ፣ አንጎላ እና ኤርትራን መጎብኘታቸው ይታወሳል።