በአደጋ ምክንያት ለዓመታት ራሱን ስቶ የቆየው ሰው የ40 ዓመት ህይወቱን ረስቶ ተነሳ
የ63 ዓመት እድሜ ያለው ይህ ሰው ራሱን የሚያየው እንደ 24 ዓመት ጎረምሳ ነው
የ30 ዓመት እድሜ ልጅ እና የልጅ ልጅ ያለው ይህ ሰው በቴክኖሎጂዎች ፍጥነት በየዕለቱ እንደተገረመ ነው ተብሏል
በአደጋ ምክንያት ለዓመታት ራሱን ስቶ የቆየው ሰው የ40 ዓመት ህይወቱን ረስቶ ተነሳ፡፡
ሉሲያኖ የተባለው ጣልያናዊ አንድ ከአምስት አመት በፊት ነበር በደረሰበት የትራፊክ አደጋ ራሱን ስቶ ወደ ሆስፒታል የገባው፡፡
የ63 ዓመት እድሜ ያለው ይህ ሰውም ከሰሞኑ ለአምስት ዓመታት ራሱን ስቶ ከቆየ በኋላ ራሱን ሊያውቅ ችሏል፡፡
ይሁንና ይህ ሰው ሚስቱን እና የ30 ዓመት ጎረምሳ ልጁን ጨምሮ ከ1983 ወዲህ ያሉ የሕይወቱን ክስተቶች እንደማያስታውስ ተገልጿል፡፡
ሉሲያኖ ለመጀመሪያ ጊዜ ለዓመታት ከቆየበት የኮማ ህይወት ሲነቃ ሚስቱ ተጠርታ ስሙን ስትጠራው “ስሜን እንዴት አወቅሽ” ሲል መልሶ ጠይቋታል ተብሏል፡፡
አደጋው በደረሰበት ወቅት ባንድ ትምህርት ቤት ውስጥ ተቀጥሮ ሲሰራ ነበር የተባለ ሲሆን እሱ ግን የሚያስታውሰው ከ20 ዓመታት በፊት በጣልያን ኤርፖርት ውስጥ የቴክኒክ ባለሙያ ሆኖ ሲሰራ የነበረውን ስራ ብቻ እንደሚያስታውስ ዴይሊ ሜይል ዘግቧል፡፡
ሉሲያኖ በወጣትነት እድሜው የሚያስታውሳት እናቱን ስም እየጠራ የት ሄደች የሚል ጥያቄ ያቀርባል የተባለ ሲሆን እናቱ ግን ከዓመታት በፊት ህይወታቸው እንዳለፈ በስርዓተ ቀብራቸው ላይ መገኘቱን ሲነገረው ለማመን ይቸገራል ተብሏል፡፡
ይህ ሰው አሁን ዘመኑ 1983 እንጂ 2024 ነው ብሎ ለመቀበል ይቸገራል የተባለ ሲሆን እንደ ጎግል ማፕ፣ ሞባይል ስልክ እና ሌሎች ዘመን አመጣሽ ቴክኖሎጂዎችን ሲያይ ይህ እንዴት ሊሆን ቻለ በማለት እንደሚገረም ተገልጿል፡፡
ስጋ እና የተቀነባበሩ ምግቦችን አብዝቶ መመገብ ለመርሳት በሽታ ያጋልጣል ተባለ
ቀንደኛ የሮማ ክለብ ደጋፊ እና የክለቡ ታሪካዊ ተጫዋች ፍራንሲስኮ ቶቲ አድናቂ ነበር የተባለው ይህ ሰው አሁን ላይ ምንም አያስታውስም፡፡
ከኮማ መንቃቱን የሰሙ ቤተሰቦቹ እና ጓደኞቹ ሊጠይቁት ሲመጡ እነማን እንደሆኑ መልሶ ይጠይቃቸዋል ተብሏል፡፡
በተለይም ራሱን በመስታወት ውስጥ ሲመለከት ይህ እሚያፈጥብኝ ሰው ማን ነው በሚል የ24 ዓመት ጎረምሳ እያለ የነበረው ሰውነቱን በመስታወት ውስጥ ለመፈለግ ሲሞክርም ታይቷል፡፡
የስነ ልቦና ባለሙያዎች የሉሲያኖን የማስታወስ ችሎታ ወደ ነበረበት ለመመለስ ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ነውም ተብሏል፡፡