ላቭሮቭ “ሂትለር አይሁዳዊ ነው” ማለታቸውን ተከትሎ እስራኤል ሩሲያ ይቅርታ እንደትል ጠይቃለች
በሩሲያ-ዩክሬን ጦርነት ጉዳይ እስራኤል ዩክሬንን ብትደግፍም ፤ ለሀገራቱ ግንኙነት ስትል ጥንቃቄ ስታደርግ ቆይታለች
እስራኤል፤ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሰርጌ ላቭሮቭ ንግግር “ጸረ ሴማዊነትና አደገኛ” ብለዋለች
እስራኤል፤ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭን የናዚ መሪ አዶልፍ ሂትለር “አይሁዳዊ ነው” ሲሉ የሰጡት አስተያየት ጸረ ሴማዊነት እና አደገኛ ነው ስትል ወቀሰች።
የእስራኤል የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያየር ላፒድ በእስራኤል የሚገኙትን የሩስያ አምባሳደር፤ ላቭሮቭ እሁድ እለት ከጣሊያን ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ስላሉት የተሳሰተ ንግግር ማብራሪያ ለመስጠት እንደሚጠሩ አስታውቀዋል።
ላፒድ ዋይ ኔት ለተባለ የዜና ድረ-ገጽ እንደተናገሩት “ይህ ይቅር የማይባል፣ አሳፋሪ መግለጫ፣ አሰቃቂ ታሪካዊ ስህተት ነው፣ እናም ከሩሲያ ይቅርታ እንጠብቃለን” ብለዋል።
እስራኤል በላቭሮቭ ንግግር እጅጉን እንደተበሳጨች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሯ በኩል ብትገልጽም፤ ከሩሲያ ኤምባሲ አስካሁን የተሰጠ ምንም አይነት አስተያየት የለም።
ሬቴ 4 ቻናል ከተባለ የጣሊያን ቴሌቭዥን ጋር በአንድ ጣሊያናዊ አስተርጓሚ አማካኝት ቆይታ ያደረጉት ላቭሮቭ፤ ስለ ሂትለር የተናገሩት ጋዜጠኛው፤ ሩሲያ አሁን በዩክሬን የምትዳርገውን ወታደራዊ ዘመቻ “ዩክሬንን ከናዚ ለማዳን” የምትለው ለምንድን ነው? ተብለው ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ ነው።
ጋዜጠኛው አስከትሎ ላቭሮቭን “የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘለንስኪ አይሁዳዊ እንደሆኑ እየታወቀ እንዴት ከናዚዝም እናድናታለን ትላላችሁ?” የሚል ጥያቄ አቅርቦላቿል።
የላቭሮቭ ምላሽ ግን “ሂትለርም እኮ አመጣጡ ከአይሁድ ነው፣ ስለዚህ ምንም ማለት አይደለም” የሚል ነበር።
ይህ ብቻ አይደለም ላቭሮቭ "ጥበበኞቹ የአይሁድ ሰዎችም፤ ትልቁ ጸረ-ሴማዊነት የሆኑት እራሳቸው አይሁዶች ናቸው ይላሉ " የሚል መከራከሪያም አቅርቧል።
የላቭሮቭ ንግግር እስራኤልን አስቆጥቷል።
እስራኤል ለዩክሬን ደጋግማ እንደምትደግፍ ገልጻላች፣ ነገር ግን በጎረቤት ሶሪያ ካበድ ተጽእኖ የመፍጠር አቅም ካላት ሩሲያ ጋር ያለው ግንኙነት እንዳይበላሽ ጥንቃቄ ስታደርግ ቆይታለች።
ለዚህም ነው ምእራባውያኑ በሩሲያ ላይ ማእቀብ ሲያዘንቡ፤ እስራኤል ድርጊቱን ከማውገዝ በዘለለ ምንም ስትል ስታስፈጽም ያልታየችው።