ፀሎተ ሀሙስ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ ተከበረ
በዓሉ በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያንና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ተከብሯል
ክርስቶስ የሃዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ በማጠብ ትህትናንና ታዛዥነት ማስተማሩን በማሰብ በዓሉ ተከብሯል
ፀሎተ ሀሙስ በክርስትና እምነት ተከታዮች ዘንድ በዛሬው እለት በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ተከብሮ ውሏል።
የፀሎተ ሀሙስ በዓል በተለይም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስ ትህትና በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ነው የተከበረው።
ክርስቶስ በዛሬዋ እለት የሃዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ በማጠብ ትህትናን እና ታዛዥነት ማስተማሩን በማሰብ ነው በዓሉ ተከብሮ የዋለው።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያን በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም የፀሎተ ሀሙስ በዓል በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ተከብሮ ውሏል።
በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል እየታከሄደ ባለው ምርሃ ግብር ላይም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስን ጨምሮ ብፁዓን ጳጳሳት፣ ቆሞሳቱ፣ ካህናና ዲያቆናት ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሚካሄደው ስነ ስርዓትም ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ የብፁዓን ጳጳሳቱን፣ ብፁዓን ጳጳሳቱ ደግሞ ቆሞሳቱ እና ካህናቱ እግር በማጠብ የኢየሱስ ክረስቶስን አርአያነት ተከትለው ስርዓቱን ፈጽመዋል።
በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንም የፀሎተ ሀሙስ በተለያዩ ኃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶች አስበው ውለዋል።