የቦርዱን አባላት ለመሰየም የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ዛሬ በምክር ቤቱ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል
ዛሬ ጥቅምት 25 ቀን 2014 ዓ/ም መደበኛ ስብሰባውን ያካሄደው 6ኛው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አቋቋመ፡፡
ምክር ቤቱ ቦርዱን ለማቋቋም በማሰብ የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ ከመረመረና ከተወያየ በኋላ በሙሉ ድምጽ አድቋል፡፡
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን አፈጻጸም የሚመረምረው ቦርድ ከምክር ቤቱ አባላትና ከህግ ባለሙያች በተውጣጡ አባላት መቋቋሙም ነው የተገለጸው፡፡
በዚህም መሰረት አቶ ለማ ተሰማ ቦርዱን በሰብሳቢነት የቀድሞዋ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈጉባዔ ወ/ሮ ወርቀሰሙ ማሞ ደግሞ በምክትል ሰብሳቢነት እንዲመሩ ተመርጠዋል፡፡
ወርቅነህ ገበየሁ፤ ጦርነቱ እንዲቆምና በአስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) የፖለቲካ ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ አቶ ሰለሞን ላሌ፣ ወ/ሮ ቢፍቲ መሐመድ፣ አቶ ምትኩ ማዳ እና አቶ ገመቹ በሻዳ ደግሞ ቦርዱን በአባልነት እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል፡፡
ተሿሚዎቹም በፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዘዳንት ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ መሪነት ቃለ መሃላ ፈጽመዋል፡፡
ምክር ቤቱ በሃገር ህልውና እና ሉዓላዊነት ላይ የተደቀነን አደጋ ለመከላከል በሚል ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ/ም በሚኒስትሮች ምክር ቤት የወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅም አጽድቋል፡፡
አዋጁ፤ አስፈላጊነቱንና ይዘቱን በተመለከተ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር አቶ ተስፋዬ በልጅጌ አጭር ማብራሪያ ካቀረቡ በኋላ ነው የጸደቀው፡፡
ሩሲያ በኢትዮጵያ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ በድጋሚ ጠየቀች
በአሁኑ ጊዜ በሀገር ህልውና ላይ የተደቀኑትን አደጋዎች በመደበኛው የህግ ማስከበር ስርዓት ለመቋቋም አዳጋች መሆኑን ያብራሩት አቶ ተስፋዬ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማወጅ እና ተግባራዊ ማድረግ አደጋውን ለመቀልበስ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ለምክር ቤቱ አብራርተዋል፡፡
የምክር ቤቱ አባላትም በአዋጁ አስፈላጊነትና በሚወሰዱ እርምጃዎች ላይ ከተወያዩ በኋላ አዋጅ ቁጥር 1264/2014 ሆኖ እንዲጸድቅ በአንድ ድምጸ ተዓቅቦ በአብላጫ ድምጽ ወስነዋል።
በመላው ኢትዮጵያ የሚተገበር ነው የተባለለት አዋጁ ለ6 ወራት እንደሚቆይ መገለጹ የሚታወስ ነው፡፡