ወርቅነህ ገበየሁ፤ ጦርነቱ እንዲቆምና በአስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ ጥሪ አቀረቡ
የኢጋድ ዋና ፀሃፊው መካረሩ ረግቦ ልዩነቶች ለሃገሪቱ ብሎም ለቀጠናው በሚበጅ መልኩ በውይይት እንዲፈቱ ጥሪ አቅርበዋል
ዶ/ር ወርቅነህ የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በከፍተኛ ስጋት እየተከታተሉ እንደሆነ አስታውቀዋል
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ዋና ፀሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ጦርነቱ እንዲቆምና አስቸኳይ ተኩስ አቁም ላይ እንዲደረስ ጥሪ አቀረቡ።
ዶ/ር ወርቅነህ የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በተመለከተ መግለጫ አውጥተዋል፡፡
በመግለጫቸው እየከረረ መጥቷል ያሉትን የኢትዮጵያ ወቅታዊ የፖለቲካ ሁኔታ በከፍተኛ ስጋት እየተከታተሉ እንደሆነ አስታውቀዋል።
ሩሲያ በኢትዮጵያ የተኩስ አቁም ስምምነት እንዲደረግ በድጋሚ ጠየቀች
ኢጋድ ጦርነቱ በተጀመረበት ወቅት ባለፈው ዓመት ሁኔታውን በማስመልከት ጥሪ ማቅረቡን ያስተወሱት ዋና ፀሃፊው ጦርነቱ እንዲቆምና በአስቸኳይ ተኩስ አቁም እንዲደረግ በድጋሚ ጥሪ አቅርበዋል።
ሁሉም ወገኖች ተቆጥበው መካረሩን እንዲያረግቡ እና ልዩነቶቻቸውን ለሃገሪቱ ብሎም ለቀጠናው በሚበጅ መልኩ በውይይት እና እርቅ እንዲፈቱም ነው ዶ/ር ወርቅነህ ጥሪ ያቀረቡት።
የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) ከወራት በፊት በዋና ጸሃፊው አብደላ ሃምዶክ በኩል የእናሸማግላችሁ ጥሪ ማቅረቡ የሚታወስ ነው፡፡
ሆኖም ኢትዮጵያ ‘የእናሸማግላችሁ’ ጥያቄ ሳትቀበል መቅረቷም አይዘነጋም፡፡