ሆቴሎች ባለመረጋጋት የደረሰባቸውን ኪሳራ ቢቋ ቋሙም ኮሮና ለጠቅላላ ኪሳራ ዳርጓቸዋል-አቶ ፍትህ
ሆቴሎች ባለመረጋጋት የደረሰባቸውን ኪሳራ ቢቋቋሙም ኮሮና ለጠቅላላ ኪሳራ ዳርጓቸዋል-አቶ ፍትህ
በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የሆቴል ዘርፉ ክፉኛ በመጎዳቱ የታክስ መክፍያ ጊዜ እንዲራዘምላቸው ለመንግስት ጥያቄ አቅርበው መልስ እየጠበቁ መሆኑን የኢትዮጵያ ሆቴልና መሰል አገልግሎቶች አሰሪዎች ፌደሬሽን ገልጿል፡፡
የፌደሬሽኑ ፕሬዘዳንት ፍትህ ወልደሰንበት ለአል-አይን አማርኛ እንደገለጹት ሆቴሎች ከገቡበት ኪስራ ለመውጣት ብዙ ጊዜ ስለሚወስድባቸው ታክስ በተራዘመ ጊዜ እንዲከፍሉ ቢደረጉ ከኪሳራ ማገገሚያ ጊዜያቸውን ያሳጥረዋል ብሏል፡፡
የሆቴሉና መሰል አገልግሎት ዘርፍ እንዲያንሰራራ፤ ፌደሬሽኙ ከታክስ ጊዜ ይራዘምልኝ በተጨማሪ ሌሎች ጥያቄዎችን አቅርቦ መልስ እየጠበቀ አንደሚገኝ አቶ ፍትህ ተናግረዋል፡፡
ብዙዎቹ ሆቴሎች በባንክ ብድር ስለተሰሩ፣ባንክ የሰጣቸው በድር ያለወለድ እንዲቆይላቸው፤ ለባንክ የሚከፍሉት ወርሀዊ የብድር ክፍያ ጊዜ አንዲራዘምና ያለወለድ ብድር እንዲሰጣቸውም መጠቃቸውን አቶ ፍትህ ገልጸዋል፡፡
መንግስት ጥያቄዎቹን እንደተቀበላቸው የገለጹት አቶ ፍትህ መልስ ግን በፈለጉት ፍጥነት እንዳልተሰጣቸው ተናግረዋል፡፡
ፕሬዘዳንት እንደገለጹት የሆቴሎች ገቢ መቀዛቀዝና ብሎም መዘጋት በዘርፉ የስራ እድል የተፈጠረላቸውን ዜጎች አደጋ ውስጥ ከቷል፡፡
አቶ ፍትህ ሆቴሎች“ለአንድ ወር የሰራተኛ ደሞዝ መክፈል አልቻልንም፤ አንድ ባለኮከብ ሆቴል በትንሹ 350 ሰዎች” ቀጥሮ ያሰራል ብለዋል፡፡
ፌደሬሽኑ 2025 ሆቴልና መሰል ድርጅቶች አባላት እንዳሉት የገለጹት አቶ ፍትህ ምን ያህል ሰራተኞች በስሩ እንዳሉ የሚያሳይ ጥናት አልተካሄደም ብለዋል፡፡
“አሁን ላይ ደግሞ ስራተኞች እንዳታሰናብቱ” የሚል መመሪያ ወጥቷል ያሉት አቶ ፍትህ የታክስ ይራዘምልኝና ሎሎች ጥያቄዎችን ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በፊት ማቅረባቸውን ገልጸዋል፡፡
አቶ ፍትህ እንዳሉት አብዛኞቹ ሆቴሎች በባክን ብድር የተሰሩ ናቸው፤ የየቀን ገቢያቸውን ለወርሀዊ የብድር ክፍያ እያዋሉት ስለሆነ እዳቸው ላይ ሊኩድ ካሽ/ የሚከፈል ብር/ እጥረት አጋጥሟቸዋል፡፡
እንደ አቶ ፍትህ ከሆነ ባለፉት አመታት በነበረው አለመረጋጋት በሆቴሎች ላይ የደረሰውን ጉዳት መቋቋም ችለው ነበር፤ ነገርግን አሁን በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት በሆቴሎችና መሰል ዘርፍ ላይ ጠቅላላ ኪሳራ ደርሷል ብለዋል፡፡
መንግስት የሆቴሎቹን ጥያቄ በምን መልኩ እንደሚያስተናግደውና ጥያቄዎችን መቼ እንደሚመልሳቸው ለመረዳት ከቱሪዝም ሚኒስቴርን የሚመለከተውንአ አካል ለማናገር ያደረግነው ሙከራ አልተሣካም፡፡
የሆቴል አገልግሎት ዘርፉ በመንግስት አይን
መንግስት የሆቴልና መሰል አገልግሎት ዘርፉን በኮረና ቫይረስ ምክንያት በከፍተኛ ደረጃ ይጎዳሉ ከሚባሉት ዘርፎችና መካከል መድቦታል፡፡
የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሽዴ ቫይረሱ በኢትዮጰያ ኢኮኖሚ ላይ የሚኖረውን ተጽእኖ ባብራሩበት ወቅት፤ የሆቴልና ቱሪዝም ጨምሮ ሁሉም ዘርፎች ተጋላጭ የሚሆኑባቸው ጉዳዮች ተለይተዋል፤ ኢኮኖሚዊ የመፍትሄ ምላሽም ተዘጋጅቷል” ብለዋል፡፡
አቶ አህመድ ተጋላጭ ለሆኑ ሴክተሮች/ዘርፎች/ በግል ንግድ ባንኮች በኩል ብድር እንዲደርሳቸው በብሄራዊ ባንክ በኩል የ15 ቢሊዮን ብር ቀርቧል መቅረቡንም ገልጸው ነበር፡፡