የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቫይረሱ በፈጠረው ተጽእኖ ሳቢያ 550 ሚሊዮን ዶላር ከሰርኩ አለ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቫይረሱ በፈጠረው ተጽእኖ ሳቢያ 550 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አጣሁ አለ
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ስራ አስፈፃሚ ተወልደ ገ/ማርያም ዛሬ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንዳሉት አየር መንገዱ በወቅታዊው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት 550 ሚሊዮን ዶላር ገቢ አጥቷል፡፡
አየር መንገዱ አሁን ላይ 90% የውጭ በረራዉን መቀነሱንም አቶ ተወልደ አስታውቀዋል፡፡ ከ 110 መዳረሻዎች የ 91 መዳረሻዎች በረራዎችን ቀንሶ በ 19 መዳረሻዎች ብቻ እየሰራ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡
ይሁንና የጭነት አገልግሎቱ እና የአውሮፕላን ጥገና ክፍሉ አሁን ላይ ጥሩ እየሰሩ መሆኑን አንስተዋል፡፡ ከቋሚ ሰራተኞች ውጭ ያሉ ሰራተኞች ለጊዜው እንዲያቆሙ አድርገናል ያሉት አቶ ተወልደ ቋሚ ሰራተኛ ላይ የተደረገም ሆነ የታሰበ ቅነሳ የለም ብለዋል ፡፡
ሌሎች አየር መንገዶች በሃገራት እየተደጎሙ ነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግን ፈተናዉን በራሱ ለመወጣት እየጣረ ነው ብለዋል። አሜሪካ ለአየር መንገድ ዘርፏ የ58ቢልዮን ዶላር ድጎማ ማድረጓን እንደ አብነት አንስተዋል፡፡
በኢትዮጵያ እስካሁን በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ከተረጋገጠ 52 ሰዎች መካከል ሶስቱ (3) የአየር መንገዱ ሰራተኞች ሲሆኑ ከእነርሱም አንዷ ማገገሟን አቶ ተወልደ መግለጻቸውን ሲጂቲኤን ጠቅሷል፡፡