የሀውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር እና በህንድ ወቅያኖስ 6 ጥቃቶች መፈጸማቸውን ገለጹ
አሜሪካ እና እንግሊዝ የሀውቲ ታጣቂዎችን ጥቃት ለመከላከል በጥምረት በታጣቂዎቹ ይዞታዎች ላይ የአየር ጥቃት እየፈጸሙ ይገኛሉ
ቡድኑ "የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ የሆነችውን ኢሰንሀወርን በቀይ ባህር ሰማናዊ ክፍል በበርካታ ሚሳይሎች እና ድሮኖች አድርገናል" ብሏል።
የሀውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር እና በህንድ ወቅያኖስ 6 ጥቃቶች መፈጸማቸውን ገለጹ።
የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች ቡድን በቀይ ባህር እና በህንድ ወቅያኖስ የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚን፣ ዩኤ ዲስትሮየርን እና ሶሰት እቃ ጫኝ መርከቦችን ኢላማ ያደረጉ ስድስት ጥቃቶች መፈጸማቸውን በኢራን የሚደገፈው ቡድን ቃል አቀባይ ያህያ ሳርኤ በትናንትናው እለት ተናግሯል።
አብዛኛው ህዝብ የሚኖርበትን የየመን ክፍል የተቆጣጠረው እና በኢራን የሚደገፈው የሀውቲ ሚሊሻ በመርከቦች ላይ ጥቃት የሚያደርሰው ከእስራኤል ጋር እየተዋጋ ላለው ሀማስ አጋርቱን ለማሳየት እንደሆነ ይገልጻል።
ቡድኑ "የአሜሪካ የጦር አውሮፕላን ተሸካሚ የሆነችውን ኢሰንሀወርን በቀይ ባህር ሰማናዊ ክፍል በበርካታ ሚሳይሎች እና ድሮኖች አድርገናል" ያለው ሳርኤ ይህ ጥቃት በ24 ሰአታት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ የተፈጸመ ነው ብሏል።
ቃል አቀባዩ አክሎ እንደገለጸው የዩኤስ ዲስትሮየር እና አብሊያኒ መርከብ ከማይና መርከብ ጋር በአንድ ላይ በሌላ ዘመቻ ኢላማ ተደርገዋል።
ከዚህ በተጨማሪም "አሎራይቅ የተባለችው መርከብም በህንድ ውቅያኖስ ጥቃት ደርሶባታል" ብሏል ቃል አቀባዩ።
የሀውቲ ታጣቂዎች ድሮኖች እና ሚሳይሎች በባብኤል ማንዴብ የባህር ወሽመጥ እና በኤደን ባህረ ሰላጤ ላይ ኢላማ ያደርጋሉ።
ሀውቲዎች እያደረሱ ያሉት ጥቃት ለመሸሽ የመርከብ ኩባንያዎች ከባለፈው ህዳር ጀምሮ ረጅሙን እና ከፍተኛ ወጭ የሚያስወጣውን በደቡብ አፍሪካ የሚዞረውን መስመር ለመጠቀም ተገደዋል።
አሜሪካ እና እንግሊዝ የሀውቲ ታጣቂዎችን ጥቃት ለመከላከል በጥምረት በታጣቂዎቹ ይዞታዎች ላይ የአየር ጥቃት እየፈጸሙ ይገኛሉ።