ፖለቲካ
የሀውቲ ታጣቂዎች ከሶሰት አመት በፊት በአቡዳቢ ላይ የፈጸሙት ጥቃት
የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች በአረብ ኢምሬትስ በንጹሃን ተቋማት ላይ ጥቃት የፈጸሙት የዛሬ ሶሰት አመት በዛሬው እለት ነበር
በአረብ ኢምሬትስ ዋና ከተማ አቡዳቢ ላይ በተፈጸመው ጥቃት ሶስት የእስያ ዜግነት ያላቸው ሶስት ንጹሃን ተገድለዋል
የሀውቲ ታጣቂዎች ከሶሰት አመት በፊት በአቡዳቢ ላይ የፈጸሙት ጥቃት ሶስት አመት ሆኖታል።
የየመን ሀውቲ ታጣቂዎች በአረብ ኢምሬትስ በንጹሃን ተቋማት ላይ ጥቃት የፈጸሙት የዛሬ ሶሰት አመት በዛሬው እለት ነበር። በአረብ ኢምሬትስ ዋና ከተማ አቡዳቢ ላይ በተፈጸመው በዚህ ጥቃት ሶስት የእስያ ዜግነት ያላቸው ሶስት ንጹሃን ተገድለዋል።
ከዚህ ዘግናኝ ጥቃት በኋላ የኢምሬትስ ጦር የሀውቲ ታጣቂዎች ጥር 24 እና 31የተኮሷቸውን ሶሰት የባለስቲክ ሚሳይሎችን ማክሸፍ ችሏል። ጦሩ የባለስቲክ ሚሳይል ማስወንጨፊያ ፓድ የመን ውስጥ ያለበትን ቦታ በመለየት ወዲያው በማውደም ምላሽ ሰጥቷል።
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አልናህያን በየአመቱ ጥር 17 የአረብ ኢምሬትስ ህዝብ አንድነትንና ጥንካሬን የሚያስታውስ ሆኗል ብለዋል።
ሸክ መሀመድ ቢን ዛይድ በኤክስ ገጻቸው "ጥር 17 የአረብ ኢምሬትስን ህዝብ አቅሮ መቆም፣ አጋርነትና ጽናት የምናስታውስበትና እነዚህን እሴቶች ቀጣይ ትውልድ እንዲመራባቸው እና ኢንደነቃቃባቸው ጠብቀን የምናቆይበት ቀን ነው" ሲሉ ጽፈዋል።