ሩሲያ እና ኢራን ስትራቴጂካዊ የትብብር ስምምነት ሊፈራረሙ ነው
ክሬሚሊን እንደገለጸው ሁለቱ መሪዎች በሶሪያ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በኢራን የኑክሌር ፕሮግራም ዙሪያ በዛሬው አለት ሊወያዩ ይችላሉ
የኢራን-ሩሲያ ትብብር ስምምነት ሞስኮ ከቤላሩስና ሰሜን ኮሪያ ካደረገችው ስምምነት እንደሚለይ ኢራን ገልጻለች
ሩሲያ እና ኢራን ስትራቴጂካዊ የትብብር ስምምነት ሊፈራረሙ ነው።
ሩሲያ እና ኢራን የጋራ ወታደራዊ ውልን ያላካተተ የስትራቴጂካዊ ትብብር ስምምነት ሊፈራረሙ መሆናቸውን ሮይተርስ የሩሲያውን ዜና አገልግሎት ታስ ጠቅሶ ዘግቧል።
"የስምምነቱ ባህሪ የተለየ ነው። እነሱ (ቤላሩስ እና ሰሜን ኮሪያ) እኛ ባላካተትናቸው በርካታ ዘርፎች ከሞስኮ ጋር ተስማምተዋል። የሀገራችን ነጻነት፣ በራስ አቅም መቆም እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው። የትኛውንም ጥምረት የመቀላቀል ፍላጎት የለንም" ሲሉ በሞስኮ የኢራን አምባሰደር ካዜም ጃላሊ ተናግረዋል።
ሩሲያ ከሰሜን ኮሪያና ቤላሩስ ጋር የጋራ ወታደራዊ ትብብርን ያካተተ ስምምነት ማድረጓ ይታወሳል። ጃላሊ ኢራን የራሷን ደህንነት ማስጠበቅ ትችላለች ብለዋል።
የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን እና የኢራኑ ፕሬዝደንት መሱድ ፔዝሽኪያን በዛሬው በሞስኮ ንግግር ካደረጉ በኋላ ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የነበረውን ስትራቴጂካዊ የትብብር ውል እንደሚፈራረሙ ክሬሚሊን ባለፈው ሰኞ እለት አስታውቋል።
ክሬሚሊን እንደገለጸው ሁለቱ መሪዎች በሶሪያ፣ በመካከለኛው ምስራቅ እና በኢራን የኑክሌር ፕሮግራም ዙሪያ በዛሬው አለት ሊወያዩ ይችላሉ።
የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት በተለይም ሞስኮ በዩክሬን ላይ ልዩ ያለችውን ዘመቻ መክፈቷን ተከትሎ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት መጠንከሩ ይገለጻል።
ክሬሚሊን ባወጣው መግለጫ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው አመታዊ የንግድ ልውውጥ በ2024 የመጀመሪያዎቹ 10 ወራት ውስጥ 15.5 በመቶ አድጓል።