ፖለቲካ
አረብ ኢምሬትስ 53ኛ አመት የውህደት በዓሏን አከበረች
መስራቹ ሼክ ዛይድ ቢን ሱልጣን አል ናህያን ባደረጉት ጥረት ነበር ከዛሬ 53 አመት በፊት በ1971 ወህደቱ የተፈጠረው
በታህሳስ 2፣1971 ፌደሬሽኑን መመስረታቸው በአረብ ኢምሬትስ ታሪክ ትልቅ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል
አሁን ላይ በመካከለኛው ምስራቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ ከሆኑ ሀገራት አንዷ የሆነችው አረብ ኢምሬትስ 53ኛ አመት የውህደት በዓሏን በዛሬው እለት አክብራለች።
መስራቹ ሼክ ዛይድ ቢን ሱልጣን አል ናህያን እና ሌሎች ገዥዎች ከዛሬ 53 አመት በፊት በ1971 ባደረጉት ታሪካ ስብሰባ ነበር ሰባት የሚሆኑ ኢምሬቶች የተዋሀዱት።
ተሰብሳቢዎቹ በውህደት ሰነድ እና በህገ በመንግሥት ላይ የፈረሙ ሲሆን መዋሀዳቸውን እና የሀገሪቱ መጠሪያሥ 'ዩናይትድ አረብ ኢምሬትስ' እንደሆነ ይፋ አደረጉ።
ይህ ታሪካዊው ስብሰባ በተመሳሳይ አመት ታህሳስ 2 የአረብ ኢምሬትስ ፌደሬሽን እንዲመሰረት ካስቻሉ ወሳኝ እርምጃዎች አንዱ ነበር።
ሟቹ ቬክ ዛይድ ቢን ሱልጣን አል ናህያን እና የኢምሬትስ ገዥዎች ባደረጉት ጥረት በታህሳስ 2፣1971 ፌደሬሽኑን መመስረታቸው በአረብ ኢምሬትስ ታሪክ ትልቅ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል።
ከፌደሬሽኑ መመሰረት በኋላ የተጀመረውኝ የስኬት ጉዞ ለማስቀጠል የአሁኑ የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝደንት ሼክ መሀመድ ቢን ዛይድ አስተዳደር "አረብ ኢምሬትስ መቶኛ አመት 2071" የሚል ግብ ነድፎ ምርጥ እና ዘመናዊ ሀገር ለመገንባት እየሰራ ይገኛል።