የሀውቲ ታጣቂዎች በቀይ ባህር በነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ ጥቃት አደረሱ
የሀውቲ ታጣቂዎች ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀነራል ያህያ ሳሬ ባወጣው ቀድሞ ሪከርድ በተደገ ቪዲዮ መግለጫ ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዷል
የአሜሪካ ማሪን አድሚኒስትሬሽን የሀውቲ ታጣቂዎች ከባለፈው ህዳር ወር ጀምሮ በመርከቦች ላይ 50 ጥቃቶችን ሰንዝረዋል ብሏል
የሀውቲ ታጣቂዎች ባስወነጨፉት የባለስቲክ ሚሳይል የፓናማ ሰንደቅ አላማ እያውለበለቀች በቀይ ባህር ስታጓዝ በነበረች ነዳጅ ጫኝ መርከብ ላይ አነስተኛ ጉዳት ማድረሳቸውን ባለስልጣናት ተናግረዋል።
ታጣቂዎቹ ከጋዛ ጦርነት ጋር በተያያዘ በቀይ ባህር በሚንቀሳቀሱ መርከቦች ላይ የሚያርሱትን ጥቃት ለአንድ ወር ያህል ጋብ ካደረጉ በኋላ ይህን ጥቃት ፈጽመዋል።
ጥቃቱ የደረሰባት ይህች መርከብ 'አንድሮሜዳ ስታር' ትሰኛለች።
የግል የጸጥታ ኩባንያው የሆነው አምብሬይ እንዳለው መርከቧ ከሩሲያ ጋር ግንኙነት ባለው ንግድ የተሰማራች ነች።
ኩባንያው እንደገለጸው ከሆነ መርከቧ ከሩሲያ ፕሪሞርስክ ተነስታ ወደ ቫዲናር ህንድ በማቅናት ላይ ነበረች ብሏል።
የሀውቲ ታጣቂዎች ቃል አቀባይ ብርጋዴር ጀነራል ያህያ ሳሬ ባወጣው ቀድሞ ሪከርድ በተደገ ቪዲዮ መግለጫ ለጥቃቱ ኃላፊነት ወስዷል።
ቃል አቀባይ እንዳሉት መርከቧ ኢላማውን የጠበቅ ምት አርፎባታል። ጥቃቱ በተፈጸመበት ወቅት የባርባዶስ ሰንደቅ አላማ ስታውለበልብ የነበረች ሌላ መርከብ በቅርብ ርቀት ላይ እንደነበረች አሜሪካ ገልጻለች።
ይህ ጥቃት የተፈጸመው ቀይ ባህር እና የኤደን ባህረ ሰላጤ በሚገናኙበት የባብኤል ማንዴብ የባህር ወሽመጥ አቅራቢያ ነው።
የሀውቲ ታጣሸቂዎች ከእስራኤል ጋር እየተዋጋ ላለው የፍልስጤሙ ታጣቂ ሀማስ አጋርነት ለማሳየት ነበር ከባለፈው ህዳር ወር ጀምሮ ከእስራኤል ጋር ግኝኙነት ያላቸውን መርከቦች እንደሚያጠቁ ያሳወቁት።
እንደአሜሪካ ማሪን አድሚኒስትሬሽን ከሆነ የሀውቲ ታጣቂዎች ከባለፈው ህዳር ወር ጀምሮ በመርከቦች ላይ 50 ጥቃቶችን ሰንዝረዋል። ታጣቂዎቹ አንድ መርከብ የያዙ ሲሆን ሌላ አንድ መርከብ ደግሞ ጉዳት በማድረስ እንድትሰጥም አድርገዋል።