በአረብ ኢምሬትስ በተካሄደው ኮፕ28 ለግብርናና ምግብ የተሰጠው ትኩረት ምን ይመስላል?
አረብ ኤሚሬትስ የሰራችው ስራ ምግብንና ግብርናን ከአየር ንብረት ጋር የማዋሃድ አስፈላጊነት ላይ ትኩረት እንዲደረግ አድርል
የምግብ ጉዳይ በኮፕ28 ጉባዔ አጀንዳዎች ውስጥ ትልቁን ትኩረት ማግኘቱ ተነግሯል
በአረብ ኢምሬትስ በተካሄደው ኮፕ28 ላይ ግብርና ልዩ ትኩረት አግኝቶ እንደነበረ በምግብ እና የመሬት አጠቃቀም ጥምረት (ኤፍ.ኦ.ኤል.ዩ) የፖሊሲ እና አለምአቀፍ ተሳትፎ ዳይሬክተር የሆኑት ኬቲ ማኩሻን ተናገሩ።
ኬቲ ማኩሻን ከአል ዐይን ኒውስ ጋር በነበራቸው ቆይታ እንደተናገሩት በኮፕ28 ላይ የምግብ ጉዳይ ትልቁን ትኩረት አግኝቶ ነበር።
በአረብ ኢምሬትስ በተካሄደው ኮፕ28 ላይ ከተደረሱ ስምምነቶች መካከል የዘላቂ የምግብ ስርዓትና ግብርና አንዱ ሲሆን 150 ሀገራት ስምምነቱን ተቀብለው መፈረማቸውም አይዘነጋም።
ጉባዔው 150 ሀገራት በፈረሙት ቀጣይነት ያለው ግብርና፣ አደጋን መቋቋም የሚያስችል የምግብ ስርዓት እና የአየር ንብረት እርምጃ የዩኤኢ ስምምነት መጠናቀቁ ኮፕ 28 ላይ ግብርና ትልቅ ትኩረት ማግነቱን እንደሚያሳይ ኬቲ ማኩሻን ተናግረዋል።
በተጨማሪም በኮፕ28 ላይ የተከበረው የምግብ ቀን መከበሩ ወሳኝ የሆኑ ውይይቶች እንዲደረጉ እና ውሳኔዎች እንዲተላለፉ እድል የሰጠ ነው ብለዋል።
ኬቲ ማኩሻን ዘላቂነት ባለው የግብርና ስምምነት ዙሪያ በሰጡት አስተያየትም፤ ይህ ስምምነት በአየር ንብረት ለውጥ ጋር ተያይዞ የምግብ ስርዓት አደጋ ላይ እንዳይወድቅ የሚያደርግ ነው ብለዋል።
እንዲህ አይነት ስምምነት ከአየር ንብረት ጋር ተያየዞ ሲፈረም በአረብ ኢምሬትስ የተካሄደው ኮፕ28 ጉባዔ የመጀመሪያ ነው ሲሉም ዳይሬክተሯ አስታውቀዋል።
የምግብ ስርዓት አጀንዳን በዚህ ገንቢ በሆነ መልኩ ትኩረት እንዲያገኝ አረብ ኢምሬትስ የሰራችውን የማስተዋወቅ ስራም እናዳንቃለን ብለዋል ኬቲ ማኩሻን።
ወደ COP29 እና COP30 ስናመራም መንግስታት በሀገር አቀፍ ደረጃ በወሰኑት ውሳኔ ላይ በቁርጠኝነት በመስራት የወደፊት ዕቅዶች ላይ በምግብ ላይ የተመሰረቱ እቅዶችን በማውጣት ወደ ትግበራ ለመግባት መንቀሳቀስ እንዳለባቸውም አሳስበዋል።
የምግብ ስርዓታችንን ዘላቂነት ያለው እንዲሁም አደጋን መቋቋም ወደሚችልመበት ደረጃ እስካላሸጋገርን ድረስ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተያዙ እቅዶቻንን ማሳካት አንንችልም ብለዋል።
ሀገራት በአረብ ኢምሬትስ የተፈረሙት ስምምነት ግብርናን እና የምግብ ስርዓትን የአየር ንብረት ለውጥ ውስጥ ፕሮግራም ውስጥ መካተት እንዳለባቸው በር የከፈተ መሆኑንም በምግብ እና የመሬት አጠቃቀም ጥምረት (ኤፍ.ኦ.ኤል.ዩ) የፖሊሲ እና አለምአቀፍ ተሳትፎ ዳይሬክተር የሆኑት ኬቲ ማኩሻን ተናረዋል።
አሁን ላይ ለአየር ንብረት ከሚበጀተው በጀት ውስጥ ለምግብ ስርዓት የሚመደበው 3 በመቶው ብቻ ነው ያሉት ማኩሻን፤ ህ በጀት በፈረንጆቹ 2030 ወደ 300 ቢሊየን ዶላር ማደግ እንዳለበትም አስታውቀዋል።
ባሳለፍነው ህዳር ወር በአረብ ኢምሬትስ ሲካሄድ የሰነበተው ኮፕ28 የአየር ንብረት ለውጥ ጉባዔ 11 ቃል ኪዳኖች እና ስምምነቶች ተፈርመውበት መጠናቀቁ ይታወሳል።
ከስምምነቶቹ መካከል የዘላቂ የምግብ ስርዓትና ግብርና ላይ የወጣው አንዱ ሲሆን 150 ሀገራት ስምምነቱን ተቀብለው መፈረማቸውም አይዘነጋም።
በተጨማሪም ኮፕ28 ጉባዔ በአየር ንብረት ለውጥ ዙሪያ ድርድር ሲደረግበት የቆየውን “የኤምሬትስ ስምምነት” በማጽደቅ መጠናቀቁም አይዘነጋም።
ከ83 ቢሊየን ዶላር በላይ የፋይናንስ ድጋፍ የተደረገበት ኮፕ28 የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመግታት ሀገራት በአንድነት ሲመክሩበትና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን ሲጠቁሙበት የቆየ ነው።