የአዕምሯችንን አቅም ለማሳደግ በቀን ምን ያክል ሰዓት የእግር ጉዞ ማድረግ ይጠበቅብናል?
ተመራማሪዎች የአዕምሮ አቅምን ለመጨመር በቀን ሊደረግ የሚገባ የእግር ጉዞ መጠን ይፋ አድርገዋል
የእግር ጉዞ ማደረግ አዕምሯችን የተሻሻ ችግር መፍታት እና የፈጠራ አቅም እንዲሁም ሚዛናዊነት እንዲላበስ ያደርጋል
ተመራማሪዎች በቀን ውስጥ ለተወሰነ ጊዜ የእግር ጉዞ ማድረግ የአዕምሯችንን አቅም ለማሳገድ እንደሚረዳ አስታወቁ።
አዲስ የተሰራ የኒውሮሳይንስ ጥናት እንዳመለከተው ከሆነ ለ20 ደቂቃ የእግር ጉዞ ማድረግ የአዕምሯችን አዲስ መረጃ ለመውሰድና ለመያዝ እንዲዘጋጅ ያደርገዋል።
በተለይም ውሳኔ ለመስጠት፣ ጭንቀትን ለመቆጣጠርና፣ በባህሪያችን ዙሪያ የሚያቅደው የአእምሯችን ክፍል ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ እንዳለው ነው ተመራማሪዎች ያስታወቁት።
ሌሎች አይነት የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች የአዕምሮ ጤናን ለመጠበቅ እንዲመረዱ የሚታወቅ ቢሆንም፤ ይህኛው ጥናት ግን የግር ጉዞ እና የየእምሮ አቅም ላይ ትኩረትን ያድረገ እንደሆነም አስታውቀዋል።
በዚህም በቀን ለ20 ደቂቃ እና ከዚያ በላይ የእግር ጉዞ ማድረግ የአእምሮን አቅም እንደሚያሳድግ እና ምንም እንቅስቃሴ ካለማድረግ የተወሰነ የእግር ጉዞ ማድረግ እንደሚሻልም ጥናቱ አመላክቷል።
ለ20 ደቂቃ በአንድ ቦታ ሳንንቀሳቀስ ስንቀመጥ እና ለ20 ደቂቃ የእግር ጉዞ ስናደርግ ያለው ልዩነትም በሚከተለው ምስል ተመላክቷል።
የሳንፎርድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ጥናቱን ባከናወኑበት ወቅት ተሳታፊዎች የእግር ጉዞ የሚያደርጉ እና የማያደርጉን በመለየት ክትትል ያደረጉ ሲሆን፤ በዚህም ለ20 ደቂቃ የእግር ጉዞ የሚያደርጉ ሰዎች ተቀምጠው ከሚውሉት የተሻለ ሆነው ተገኝተዋል።
ተመራማሪዎች የአእምሮ እንቅስቃሴን በኤሌክትሮኤንሴፋሎግራፊ (ኢኢጂ) መለካት ምን እየተፈጠረ እንዳለ የተመለከቱ ሲሆን፤ በዚህም የእግር ጉዞ የሚያደርጉ ሰዎች ላይ ተጨባጭ እና አወንታዊ ተፅእኖዎችን አይተዋል።
የትላልቅ የቴክኖሎጂ ኩባንያ መስራችና ባለቤቶች ከመቀመጥ ይልቅ እየተራመዱ ስብሰባ ማድረግን እንደሚመርጡም ጥናቱ ለአብነት አስቀምጧል።
ከእነዚህም ውስጥ የፌስቡክ መስረችና ባለቤት ማርክ ዙከርበርግ እና የአፕል ኩባያው ስቲቭ ጆብስ ስብሰባን ቁጭ ብሎ ከማድረግ ይልቅ እየተራመዱ ማካሄድን በማበረታታት ይታወቃሉ ተብሏል።
የዘመናዊ መድሃኒት አባት ተብሎ የሚታወቀው ሂፖክራትስም የእግር ጉዞ “የሰው ልጆች ምርጡ መድሃኒት” ብሎ እንደሚገልጸውም ነው ተመራማሪዎቹ ያስታወቁት።
እንቅስቃሴ ማድረግ የአእምሮ አቅምን እና ጤናን ከማጠናከር በተጨማሪም የልብ እና ሳንባ ጤናን ለመጠበቅ እና አጥንቶችን ለማጠንከር እንዲሁም የምግብ መፈጨትን እና የደም ስኳርን ለማስተካልም ይረዳል።