ኔታንያሁ ሃማሰ በየቀኑ 10 ታጋቾችን የሚለቅ ከሆነ በታጋቾቹ መጠን የተኩስ ቁሙ ሊራዘም ይችላል ብለዋል
እስራኤልና ሃማስ በጋዛ ለአራት ቀናት የተኩስ አቁም ለማድረግ የደረሱት ስምምነት በዛሬው እለት ይጠናቀቃል።
የተኩስ አቁም ስምምነቱ ዛሬ 4ኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን፤ ለአራት ቀናት በሚቆየው ስምምነቱ ሃማስ 50 ታጋቾችን እንደሚለቅ፤ በአንጻሩ እስራኤል ደግሞ 150 እሰረኞችን እንደምትለቅ ይጠበቃል።
በተኩስ አቁም እምምነቱ መሰረት እስካሁን 175 ሰዎች ከእገታና ከእስር ተለቀዋል።
በ4ኛ ቀን የተኩስ አቁም ስምምነቱ እስካሁን ምን ተካሄደ፤ ምንስ ይጠበቃል?
የአራት ቀን የተኩስ አቁም ከተጀመረበት አርብ አንስቶ በሶስት ዙር የእስረኛ እና ታጋቾች ልውውጥ ተካሂዷል።
እስካሁን በድምሩ 175 ሰዎች ከሁለቱም ወገን ተለቀዋል፤ ከተለቀቁት መካከልም፤
39 የእስራኤል ዜጎች በሃማስ ተለቀዋል፤ ይህም በ3 ዙር የተካሄደ ሲሆን፤ በእያንዳንዱ ዙር 13 ሰዎች ተለዋል።
117 ሊስጤማውያን እስረኞች በእስራኤል ከእስር ተለቃዋል፤ ይህም በ3 ዙር የተካሄደ ሲሆን፤ በእያንዳንዱ ዙር 39 ሰዎች ተለዋል።
17 የታይላንድ ዜጎች ከሃማስ እገታ ተለቀዋል
አንድ የፊሊፒንስ ዜጋ እንዲሁም
አንድ የእስራኤል-ሩሲያ ዝግነት ያለው ሰው ተለቋል።
የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን በዛሬው እለት ሃማስ የሚለቃቸውን የታጋቾች ዘርዝር እስራኤል እንደመትቀበል በመዘገብ ላይ ይገኛሉ።
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ሃማስ በየእለቱ በአማካኝ 10 ታጋቾችን የሚለቅ ከሆነ ታጋቾቹ ተለቀው እስኪያልቁ ድረስ የተኩስ አቁሙን ለማስቀጠል ይቻላል ብለዋል።
ሃማስም የታወጀው የተኩስ አቁም እንዲራዘም በመጠየቅ ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል።
አሜሪካ፣ ግብጽ እና ኳታር ለአራት ቀናት የታወጀው እና በዛሬው እለት የሚጠናቀቀው የተኩስ አቁም እንዲራዘም ጫና በመፍጠር ላይ ይገኛሉ ተብሏል።