ትራምፕ ስደተኞች "ደማችንን እየበከሉ ነው" የሚለውን ንግግራቸውን ደገሙት
ትራምፕ ይህ ያሉት ከሜክሲኮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች በሚገቡበት ኒው ሄሚስፌር ግዛት ባደረጉት የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ነው
የያሌ ፕሮፌሰር እና በዘረኝነት ጉዳይ መጸሀፍ ያሳተሙት ጆናታን ስታንሊ ትራምፕ ቋንቋውን ደግመው መጠቀማቸው አደገኛ ነው ብለዋል
ትራምፕ ስደተኞች "ደማችንን እየበከሉ ነው" የሚለውን ንግግራቸውን ደግመውታል።
ሪፐብሊካንን በመወከል ለፕሬዝዳንትነት የሚወዳደሩት ዶናልድ ትራምፕ ስደተኞች "የሀገራችንን ደም እየበከሉ ነው" በማለት ከዚህ በፊት በዘረኝነት እና የናዚን መፈክር በማስተጋባት ትችት ያስነሳባቸውን ንግግር ደግመውታል።
ትራምፕ ይህ ያሉት ከሜክሲኮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች በሚገቡበት ኒው ሄሚስፌር ግዛት ባደረጉት የምርጫ ቅስቀሳ ላይ ነው።
ትራምፕ ለአራት አመት የስልጣን ዘመን በድጋሚ የሚመረጡ ከሆነ በህገወጥ ስደትን እንደሚያስቆሙ እና በህጋዊ ሰደተኞች ላይ ደግሞ ጥብቅ ቁጥጥር እንደሚያደርጉ ተናገረዋል።
ትራምፕ ለደጋፊዎቻቸው ስደተኞች ከደቡብ አሜሪካ በተጨማሪ ከአፍሪካ፣ ከእስያ እየመጡ ነው ሲሉ ተያግረዋል።
"ከሁሉም የአለም ክፍል ወደ ሀገራችን የፈሰሱ ነው"
ትራምፕ ናሽናል ፐልስ ከተባለው የቀኝ ዘመም ዌብሳይት ጋር ባለፈው መስከረም ወር መጨረሻ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ስደተኞች "ደማችንን እየበከሉት ነው"የሚል ተመሳሳይ ንግግር አሰምተው ነበር።
በወቅቱ ይህ የትራምፕ ንግግር "ዘረኝነት እና ጥላቻ" የሚያንጸባርቅ ነው የሚል ትችት አስነስቶ ነበር።
የያሌ ፕሮፌሰር እና በዘረኝነት ጉዳይ መጸሀፍ ያሳተሙት ጆናታን ስታንሊ ትራምፕ ቋንቋውን ደግመው መጠቀማቸው አደገኛ ነው ብለዋል።
ፕሮሬሰሩ እንደተናገሩት ትራምፕ የጀርመኖች ደም በደዊሾች እየተበከለ ነው የሚለውን የሂትለር ንግግር ያስተጋባ ነው ሲሉ ተችተውታል።
ስታሊ"ትራሞፕ ይህ ቃል በሁሉም የድጋፍ ሰልፎች ላይ እየደገሙት ነው። አደገኛ የሆኑ ንግግሮችን መደጋገም እንዲለመዱ ያደረጋል" ብለዋል።
ፕሮፌሰሩ እንደተናገሩት ይህ በአሜሪካ በሚኖሩ ስደተኞችን ስጋት ላይ እንዲወድቁ ያደርጋል።
ባለፈው ጥቅምት ወር የትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ቃል አቀባይ ስቴቨን ቹንግ እንዲህ አይነት ቃላት በመጽሀፍ፣ በዜና እና በቴሌቪዥን የተለመድ ናቸው በማለት በትራምፕ የቀረበውን ትችት "ትርጉም የለሽ" ሲሉ አጣጥለውት ነበር።