የሰው ልጅ በእድሜ ዘመኑ ረጅም ጊዜ የሚያጠፋባቸው ተግባራት (በአመት)
ስራ ፣ እንቅል እና መመገብ ሰዎች ከቀናቸው 80-90 በመቶ የሚሆነውን ክፍል የሚያሳልፉባቸው ተግባራት ናቸው
ለሁሉም ሰው በቀን 24 ሰዓት በአመት 365 ቀን እኩል ቢሰጠውም እንደየቦታው እና አካባቢው ሰዎች የእድሜያቸውን በርካታ ክፍል የሚያሳልፉባቸው ተግባራት ይለያያሉ
በምድር ላይ የመጨረሻው ውድ እና ውስን ሀብት እንደሆነ የሚነገርለት ጊዜ ለሁሉም ሰው በተመሳሳይ መዋቅር ተከፋፍሎ የተሰጠ ነው፡፡
በቀን 24 ሰዓታት ፣ በዓመት 365 ቀናት ፣ በድምሩ 8,760 ሰዓታት በአመት ቢኖሩም ሰዎች የጊዜያቸውን በርካታ ክፍል የሚያሳልፉባቸው ተግባራት በቦታ እና አካባቢ ይለያሉ፡፡
መተኛች፣ መስራት ፣ መብላት ፣ የቤት ውስጥ ስራ እና መዝናናት ብዙ ሰዎች በተደጋጋሚ የሚያደርጓችው ተግባራት ቢሆንም ሰዎች ከፍተኛ ዋጋ በሚሰጧቸው ነገሮች ላይ ጊዜ ለማሳለፍ በሚኖራቸው ነፃነት ላይ ልዩነቶችም አሉ፡፡
በአለም ዙሪያ ያሉ ሰዎች ጊዜያቸውን እንዴት እንደሚያሳልፉ ለማወቅ የሚደረግ የኑሮ ሁኔታዎችን፣ ኢኮኖሚያዊ ጥንካሬን እና አጠቃላይ ደህንነትን ግምት ውስጥ ያስገባ ሊሆን ይገባል፡፡
“አወር ወርልድ ኢን ዳታ” የተሰኝው የጥናት ተቋም ሰዎች የቀናቸውን ብዙ ክፍል በምን አይነት ተደጋጋሚ እንቅስቃሴዎች ላይ ያሳልፉታል በሚል ባደረገው ጥናት፤ አንድ ቀን የመመገቢያ ፣ የመተኛ ፣ የስራ እና የመዝናኛ ጊዜ ተብሎ በብዙ ሰዎች ዘንድ እንደሚከፋፈል አስቀምጧል፡፡
ለነዚህ እንቅስቃሴዎች ደግሞ ከቀን ውስጥ ከ80-90 በመቶ ጊዜን ወይም በቀን 1440 ደቂቃዎች እንደሚያልፉ አመላክቷል፡፡
በዚህም በአማካኝ የሰው ልጅ በእድሜ ዘመኑ ረጅም ጊዜ ከሚያጠፋባቸው ተግባራት መካከል እንቅልፍ አንዱ ሲሆን ለመኝታ 26 አመታት እንደሚውሉ ተነግሯል፡፡
ከእንቅልፍ ቀጥሎ የሰው ልጅ የአማካኝ እድሜውን 12 አመታት የሚያውለው ስራ ላይ በሚያሳልፈው ጊዜ ነው ተብሏል፡፡
ቴሌቪዝን መመልከት ፣ ገበያ መገበያየት ፣ መብላት እና መጠጣት ከ8.8 – 3.6 አመት የሚወሰዱ ተግባራት መሆናቸው በጥናቱ ላይ ተመላክቷል፡፡
በአንጻሩ ለመሳቅ 240 ቀናት ለማልቀስ ደግሞ 30 ሰአታትን ሰዎች ከእድሜያቸው ላይ ያውላሉ፡፡