ታይላንድ በሀማስ የታገቱ ዜጎቿን እንዴት ማስለቀቅ ቻለች?
በትናንትናው እለት ሶስት የታይ ዜጎች ሲለቀቁ በአጠቃላይ ከእገታ የተለቀቁ የታይ ዜጎች ቁጥር ወደ 17 ከፍ ብሏል
"ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ የታይ ታጋቾች እንዲለቀቁ ሀማስን በማነጋገር ብቸኞች ነበርን" ሲሉ የታይ አሉምኒ ማህበር ፕሬዝደንት ለርፖንግ ሰይድ ተናግረዋል
በኳታር አደራዳሪነት ተኩስ ያቆሙት ሀማስ እና እስራኤል ታጋቾችን በእስረኞች ተቀያይረዋል።
ታይላንድም ዜጎቿን ከእገታ ለማስለቀቅ ከፍልስጤሙ ቡድን ጋር የራሷ የሆነ ስምምነት አድርጋለች።
በትናንትናው እለት ሶስት የታይ ዜጎች ሲለቀቁ በአጠቃላይ ከእገታ የተለቀቁ የታይ ዜጎች ቁጥር ወደ 17 ከፍ ብሏል።
ይፋዊ የሆነ ንግግር የተጀመረው የታይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባለፈው ጥቅምት ወር ኳታርን ከጎበኙ በኋላ መሆኑን ስኳይ ኒውስ ምንጮችን ጠቅሶ ዘግቧል።
"ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ የታይ ታጋቾች እንዲለቀቁ ሀማስን በማነጋገር ብቸኞች ነበርን" ሲሉ የታይ አሉምኒ ማህበር ፕሬዝደንት ለርፖንግ ሰይድ ተናግረዋል።
ለርፖንግ እንደተናገሩት"ታይላንድ በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ላይ ብቻ ብትንጠለጠል ወይምን የሌሎች ሀገራትን እርዳታ ብትጠይቅ በመጀመሪያው ዙር የመለቀቅ እድላቸው ዝግተኛ ይሆን ነበር"
የታይ ታጋቾች ከተለቀቁ በኋላ በእስራኤል ሻሚር ሜዲካል ማዕከል መገናኘታቸውን የታይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገልጿል።
ለርፖንግ ባለፈው ጥቅምት ወር ወደ ኢራን ተጉዘው የሀማስ ተወካዮችን ያናገረው የታይ ሙስሊም ቡድን አባል ናቸው ተብሏል።
ይህ ይፋዊ ድርድር ባይሆንም የታይ መንግስት አልተቃወመውም።
ልላኛው የቡድኑ አባል እና የቀድሞ ፖለቲከኛ አሪፐን ኡታራሲ "የኛ ቡድን ወደ ኢራን በመሄድ ከሀማስ ጋር በቀጥታ ማውራታችን ወሰኝ ነበር"ብሏል።
ለርፖንግ እንደገለጹት ወደ ኢራን የተጓዘው ቡድን ከሀማስ ባደረገው የሶስት ሰአታት ውይይት የታይ ዜጎች የግጭቱ አካል ባለመሆናቸው ሊለቀቁ እንደሚገባ አስረድተዋል።
በወቅቱ ሀማስም ተኩስ አቁም ሲደረግ ያለቅድመ ሁኔታ እንደሚለቃቸው እንዳረጋጠላቸው ሊልፖንግ ተናግረዋል።
ኢራን የታይ ዜጎች እንዲለቀቁ ጥረት ማድረጓን ብትገልጽም፣ ሀማስ ግን የተለቀቁት በቱርኩ ፕሬዝደንት ኢርዶጋን ጥረት ነው ብሏል።
ከጦርነቱ በፊት 30ሺ የሚሆኑ የታይ ዜጎች በዋናነት በግብርና ዘርፉ ተሰማርተው ይሰሩ ነበር።