በእጅ ስልካችን ላይ ባሉ መተግበሪያዎች እንዳንሰለል ምን ማድረግ አለብን?
መረጃ መንታፊዎች ህይወትን ለማቅለል የተሰሩ መተግበሪያዎችን ተጠቅመው ጥብቅ የሚባሉ መረጃዎቻችን ሳይቀር ይወስዳሉ
በርካቶች ስልካቸው ካለማወቅ አልያም ጉዳቶችን ችላ በማለት ምክንያት የግል እንቅስቃሴያቸውን አሳልፈው ለሶስተኛ ወገን ይሰጣሉ
በእጅ ስልካችን ላይ ባሉ መተግበሪያዎች እንዳንሰለል ምን ማድረግ አለብን?
በየዕለቱ ህይወታችንን የሚያቀሉ ቴክኖሎጂዎች እየተፈበረኩ ሲሆን ሰዎች በነዚህ ውጤቶች ድካማቸውን አቅልለዋል፡፡
ይህ ጥቅም እንዳለ ሆኖ ግን እነዚህን መተግበሪያዎችን በመጠቀም ለተለያዩ አገልግሎቶች የሚውሉ መረጃዎቻችንን ይወስዳሉ፡፡
ለአብነትም መተግበሪያዎች የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችንን ማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች አሳልፎ መስጠጥ፣ የማስታወቂያ ድርጅቶች የገንዘብ ልውውጣችን ማወቅ፣ የመሸመት አቅማችንን፣ ዝንባሌያችንን እና ሌሎች ፍላጎቶቻችን ለማወቅ ይጠቅማሉ፡፡
ይህን ተከትሎ እንደ ቀልድ በእጅ ስልከችን ላይ ያወረድናቸው መተግበሪያዎች ከዋና አገልግሎቶቻቸው በተጨማሪ ያለ እኛ ፈቃድ ወይም ጉዳት አያመጡብንም በሚል አመለካከት መረጃዎቻችን እንዲወስዱ ፈቃድ ይወስዳሉ፡፡
ታዋቂው የበይነ መረብ ደህንነት ባለሙያው ዳረን ጉሲዮን ለኤኤአፍፒ እንዳሉት ሰዎች ስልካቸውን በሚገባ እንዲቆጣጠሩ አሳስበዋል፡፡
በተለይም ያለንበትን አካባቢ ወይም የአድራሻ መረጃን ለማንኛውም መተግበሪያ ፈቃድ ሊሰጥ አይገባም የሚሉት ባለሙያው ያለንበት አካባቢ ማለት ለማንኛውም ጥቃት መሰረት መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የግድ አገልግሎት ለማግኘት አስፈላጊ ከሆነ ብቻ የአካባቢ ወይም ሎኬሽንን መፍቀድ እንደሚያስፈልግም አክለዋል፡፡
ያለንበት አካባቢ ማለት የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ማስታወቂያ ለመልቀቅ፣ አንዳንዴ ከራሳችን ውጪ ሌላ ሰው እንዳያውቅብን ወደ ምንፈልገው ቦታ መሄድ ቢኖርብን፣ የምንጠቀመውን ኢንተርኔት፣ ብሉቱዝ፣ ዋይፋይ እና ሌሎች ተያያዥ መረጃዎችን አሳልፎ ለመስጠት ዋነኛው ነውም ብለዋል፡፡
በብዙዎቻችን ስልክ ላይ ያሉት ሁሉም መተግበሪያዎች ቢችሉ አድራሻችንን መውሰድ ይፈልጋሉ የሚሉት ባለሙያው ነገር ግን ሰዎች በየጊዜው ስልካቸውን ቶሎ ቶሎ መፈተሸ፣ የማያውቋቸውን እና የማይጠቀሟቸውን መተግበሪያዎች ማጥፋት፣ ያለፈቃዳቸው አድራሻቸውን እየወሰዱ ያሉ መተግበሪያዎችን ፈቃድ መከልከል ይጠበቅባቸዋልም ተብሏል፡፡
እንዲሁም አድራሻ መውሰድን ዋነኛ ግባቸው ከሚያደርጉ የጎግል መተግበሪያዎች ይልቅ ሌሎች የኢንተርኔት አገልግሎቶችን መጠቀም መልመድ እንደሚስፈልግም ተገልጿል፡፡