የአሜሪካ ፕሬዝዳንት በ538 ወኪል መራጮች አማካኝነት በቀጥታ ይመረጣል
አሜሪካዊያን ፕሬዝዳንታቸውን በቀጥታ መምረጥ እንደማይችሉ ያውቃሉ?
በዓለማችን ካሉ ዲሞክራሲያዊ ሀገራ መካከል አንዷ እንደሆነች የሚታመነው አሜሪካ የቀጣዩ አራት ዓመታት መሪን ለመምረጥ የመጨረሻ ቀን ላይ እንገኛለን፡፡
ከ160 ሚሊዮን በላይ መራጮች ድምጻቸውን ይሰጡበታል የተባለው ይህ ምርጫ በመላው ዓለም ትኩረትን ስቧል፡፡
ይህ ምርጫ እንዴት ይካሄዳል? ዜጎችስ ፕሬዝዳንታቸውን እንዴት ነው የሚመርጡት?
ሀገሪቱ ምርጫን ስታካሂድ 200 ዓመት የሆናት ሲሆን ዜጎች ፕሬዝዳንታቸውን በተዘዋዋሪ እንደሚመርጡ የሀገሪቱ ምርጫ ህግ ያስረዳል፡፡
መራጭ አሜሪካዊያን የሚፈልጉትን እጩ ፕሬዝዳንት መምረጣቸውን የሚያሳይ ሰነድ በተዘጋጀላቸው የድምጽ መስጫ ቦታ የሚመርጡ ሲሆን የመራጮችን ፍላጎት በማየት ወኪል መራጮች ደግሞ ፕሬዝዳንቱን በቀጥታ መርጣሉ፡፡
በዚህ የምርጫ ህግ መሰረት አሜሪካዊያን ፓርቲዎችን ወክለው በየግዛቱ በተመረጡ ወኪል መራጮች ወይም ኢሎክቶራል ኮሌጅ አማካኝነት ፕሬዝዳንታቸውን ይመርጣሉ፡፡
በምርጫው የሚሳተፉ ፓርቲዎችን ወክለው የሚመረጡ የመራጭ ወኪሎች በተለያዩ መንገዶች የሚመረጡ ሲሆን በግዛቶቹ ወይም ክልሎች ስር ያሉ መራጮችን ወክለው ፕሬዝዳንቱን ይመርጣሉ፡፡
በዚህ የሀገሪቱ ህግ መሰረት አሜሪካዊን ፕሬዝዳንታቸውን በሁለት መንገድ መምረጥ የሚችሉ ሲሆን የመጀመሪያው ፓርቲዎችን ወክለው ከየግዛቱ በተመረጡ ወኪሎች አማካኝነት የሚመርጡ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እጩ ፕሬዝዳንቶች እኩል ድምጽ አግኝተው ማሸነፍ ካልቻሉ ደግሞ ከየግዛቱ ለሀገሪቱ ህግ አውጪ ምክር ቤት ወይም ሴኔት አማካኝነት በሚሰጥ ድምጽ ፕሬዝዳንት ይመረጣል፡፡
እንደ ሀገሪቱ ምርጫ ህግ መሰረት አሜሪካ 538 ወኪል መራጮች ያሏት ሲሆን እጩዎች ምርጫውን ለማሸነፍ በትንሹ 270 የወኪል መራጮችን ድምጽ ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡
እጩ ተወዳዳሪዎች ዝቅተኛ የወኪል መራጮች ድምጽ የሚባለው 270 ድምጽ ማግኘት ካልቻሉ አዲስ የተመረጡት የህግ አውጪ ምክር ቤት አባላት በሚያደርጉት አስቸኳይ ምርጫ የሀገሪቱን ፕሬዝዳንት እንዲመርጡ የአሜሪካ ህገ መንግስት ያስገድዳል፡፡
የወኪል መራጮች ድምጽ ከግዛት ግዛት የሚለያይ ሲሆን ካሊፎርኒያ ከሁሉም የአሜሪካ ግዛቶች ከፍተኛውን ድርሻ ትይዛለች፡፡
ከ48-50 ግዛቶች ላይ የተከፋፈለው የወኪል መራጮች ድምጽ ድርሻ ወይም ብዛት በየ 10 ዓመቱ እንደሚከለስ የሀገሪቱ የምርጫ ህግ ያስገድዳል፡፡
የወኪል መራጮች ድምጽ አሰጣጥ ሂደት አሸንፏል የተባለው እጩ ፕሬዝዳንት በይፋ ስልጣን ከመረከቡ በፊት የድምጽ አሰጣጥ ሂደቱ ትክክል መሆኑ በሀገሪቱ ህግ አውጪ ምክር ቤት መጽደቅ አለበት፡፡