በኳታር የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እያየሉ ነው ተባለ
ለ 2022 የዓለም ዋንጫ ዝግጅት የሚሠሩ ሠራተኞች ስለሚፈጸምባቸው የመብት ጥሰቶች የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ብዙ ብለዋል
በተለይ በሀገሪቱ በሚኖሩ የውጭ ሰራተኞች ላይ በህግ ጭምር የተደገፈ የመብት ጥሰት ይፈጸማል
“ኳታር የሰብዓዊ መብቶችን ፣ የሕግ የበላይነትን እና የሥርዓተ-ፆታ እኩልነትን ለማክበር ቁርጠኛ መሆኗን እናረጋግጣለን” በተባበሩት መንግስታት የኳታር ተወካይ በቅርቡ ያደረጉት ንግግር ነው፡፡
ይህ የኳታር ፣ የሰብአዊ መብቶች ተሟጋች እና የሥርዓተ-ፆታ እኩልነት መርህ ፈፃሚ በመምሰል የመቅረብ ፣አዝማሚያ የሰብአዊ መብቶችን እና የጾታ አድሎአዊነትን በመጣስ የሰፈረችበትን ጥቁር መዝገብ በመርሳት ራሷን ለዓለም ለማስተዋወቅ የምታደርገው ሙከራ እንደሆነ በብዙዎች ይታመናል፡፡
ይሁንና የኳታር የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ከዓለም ፊት የተደበቁ አይደሉም፡፡
የሰብአዊ መብት ጥሰቶች
ምናልባትም ዓለም ስለ ኳታር የሰብአዊ መብት ጥሰት በይበልጥ የሚያውቀው ፣ የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ባለፈው ግንቦት በጄኔቫ በተካሔደው ሠላሳ ሦስተኛው ስብሰባ ላይ ስለ ኳታር አገዛዝ የሰብአዊ መብቶች ጥሰትይፋ ያደረጉትን አንዳንድ አሳፋሪ ድርጊቶች ነው፡፡
የተባበሩት መንግስታት ሪፖርት እንዳመለከተው “የኳታር ፍ / ቤቶች በዜጎች እና በውጭ ዜጎች ላይ የሚያደርጉት አያያዝ እንደ ግለሰቦቹ ዜግነት ፣ ኢኮኖሚያዊ ወይም ሙያዊ ደረጃ የሚለያይ ሲሆን በተጨማሪም የ 2005 የኳታር የዜግነት ህግ ቁጥር (38) ደግሞ በህግ ሂደት የሀገሪቱ ዜጋ የሆኑ ሰዎች አነስተኛ ጥበቃ እንዳላቸው ይደነግጋል!”
ሪፖርቱ አክሎም “በኳታር ውስጥ በውጭ ዜጎች ዘንድ በስፋት እየተስተዋለ ያለው አመለካከት ፍ /ቤቶች የኳታር ዜጎችን በእኩል አያዩም ፣ የውጭ ዜጎችም በእኩል አይስተናገዱም ፣ በተጨማሪም እንደየሰው ዜግነት ወይም ኢኮኖሚያዊ እና ሙያዊ ሁኔታ ሊለያይ ይችላል” የሚል ነው፡፡
የሰራተኞች መብቶች
በ 2022 በኳታር ለሚካሔደው የዓለም ዋንጫ ዝግጅት የተለያዩ ስራዎችን የሚሠሩ ሠራተኞች ስለሚፈጸምባቸው የሰብአዊ መብት ጥሰቶች ዓለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች አስከፊ ታሪኮችን ዘግበዋል፡፡
የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ዘገባዎች ዶሃ በሰራተኞች ላይ የፈፀመችውን ሰፊ ጥሰት ያሳያል፡፡ የኳታር መንግስት ፖሊሲ በውጭ ሰራተኞች መብቶች ላይ የሚፈጸመው በደል ህንፃዎችን በተያዘው ጊዜ ከማጠናቀቅ አንጻር ሲታይ “የሁለተኛ ደረጃ ጉዳይ” መሆኑን ያንጸባርቃል፡፡
ከውጭ ሰራተኞች ቀጣይነት ያለው የመብት ጥሰት ጋር በተያያዘ ከ 7 ዓመታት በላይ ዓለም አቀፍ ምርመራዎች የተደረጉ ሲሆን ኳታር የ2022 የዓለም ዋንጫን እንዳታስተናግድ በርካታ ጥያቄዎች ተነስተውባታል፡፡
በአውሮፓውያኑ 2020 መጀመሪያ ኳታር የዓለም ዋንጫን ለማዘጋጀት በሚደረጉ ግምባታዎች ላይ ለሚሳተፉ ሰራተኞች የመከላከያ ጥንቃቄ ባለመኖሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራተኞች በኮሮናቫይረስ መያዛቸው ተገልጿል፡፡
የውጭ ሰራተኞች እዚያ እያጋጠሟቸው ስላለው አስቸጋሪ ሁኔታ በዝርዝር ያብራሩ የውጭ ጋዜጦች ዘገባዎች ባይተላለፉ ኖሮ ዶሃ እነዚህን ጉዳቶች ባላወጀ ነበር ፡፡
ከዚህ ጋር ተያያዥነት ባለው ሁኔታ አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጥቅምት 20 ባወጣው ዘገባ የውጭ የቤት ሰራተኞች በኳታር የሚደርስባቸውን ግፍ ሲያጋልጥ እጅግ ከባድ በሆነ የሥራ ሁኔታ እንደሚሰቃዩ ያረጋገጠ ሲሆን አንዳንዶቹም ድብደባ ፣ ወሲባዊ ትንኮሳ እና አስገድዶ መድፈር ደርሶባቸዋል ብሏል፡፡
ድርጅቱ ሪፖርቱን ያቀረበው ከ 105 ሴቶች ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ሲሆን ወደ 85 በመቶ የሚሆኑት የእረፍት ቀን እንደማይሰጣቸው ወይም በጭራሽ እንደማያውቁ እና አሰሪዎቻቸው ፓስፖርታቸውን ተቀብለዋቸው ራሳቸው ጋር እንደሚያደርጉ ተናግረዋል፡፡