ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የቀድሞውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪን ቀጣዩ የአየር ንብረት መልዕክተኛ አድርገው ሰየሙ
ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን የቀድሞውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪን ቀጣዩ የአየር ንብረት መልዕክተኛ አድርገው ሰየሙ
ከአራት ዓመታት በፊት የፓሪሱን የአየር ንብረት ስምምነት የፈረሙት ጆን ኬሪ አሁን ወደ ኃላፊነት መመለሳቸው ተመራጩ ፕሬዚዳንት ለአየር ንብረት ለውጥ ትኩረት እንደሰጡ ያመለክታል ተብሏል፡፡
ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካን ከፓሪሱ የአየር ንብረት ስምምነት ቢያስወጧትም ተመራጩ ፕሬዚዳንት ግን ወደ ሥምምነቱ እንደሚመልሷት ይጠበቃል፡፡ በአሜሪካ ከፍተኛ ሥልጣን ላይ የነበሩትን ጆን ኬሪን ለዚህ ኃላፊነት ማጨታቸውም ለዚህ ማሳያ ነው ተብሏል፡፡ኬሪ ከፓሪሱ የአየር ንብረት ስምምነት በተጨማሪም የኢራን ኒዩክለር ስምምነት ላይም ጉልህ ሚና የነበራቸው ባለስልጣን ናቸው፡፡
በአዲሱ የኃላፊነት ቦታቸው የአየር ንብረት የሚያስከትለውን ችግር ለመቋቋም የሙሉ ጊዜ ሥራ እንደሚሰሩ ይጠበቃል፡፡ በዚህም መሰረት ጆን ኬሪ አየር ንብረትን በተመለከተ በብሔራዊ የጸጥታ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ አሜሪካን ከፓሪሱ የአየር ንብረት ስምምነት የወጣች የመጀመሪ ሀገር ቢያደርጓትም ተመራጩ ጆ ባይደን ወደ ስምምነቱ እንደሚመልሷት ይጠበቃል፡፡
ጆ ባይደን ልክ እንደ ምክትል ፕሬዚዳንታቸው ካማላ ሀሪስ ሁሉ የገንዘብ ሚኒስትራቸውንም ሴት ሊያደርጉ እንደሆነ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ በዚህም መሰረት የቀድሞዋ የፌዴራል ግምጃ ቤት ኃላፊ ጃኔት ያለን የገንዘብ ሚኒስትር እንደሚሆኑ እየተገለጸ ነው፡፡
በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ስምምነት በማዘጋጀትና በማስተባበር ላይ የነበሩት የአሜሪካ የገንዘብ ሚኒስትር ስቲቭ ሙኑችን በጃኔት ያለንእንደሚተኩ የወጡ ሪፖርቶች ወጥተዋል፡፡