ሸሽተው የነበሩት የባንግላንዴሻ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ልጃቸው ተናገረ
ሁሲና ባለፈው ሰኞ ወደ ጎረቤት ህንድ የሸሹት ለሳምንታት የቆየው ብርቱ ህዝባዊ ተቃውሞ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ስላስገደዳቸው ነው
ሁሲና አሁን ላይ ህንድ ውስጥ ጥበቃ በሚደረግለት ቤት ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል
ሸሽተው የነበሩት የባንግላንዴሻ ጠቅላይ ሚኒስትር ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ልጃቸው ተናገረ
የቀድሞ የባንግላዴሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሸኪህ ሁሲና የሀገሪቱ ጊዜያዊ መንግስት ምርጫ ለማካሄደ በሚወስንበት ወቅት ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱ ልጃቸው ተናግራል።
ነገርግን ሁሲና በምርጫ ለመሳተፍ ስለመፈለጋቸው ግልጽ አልሆነም።
ሁሲና ባለፈው ሰኞ ወደ ጎረቤት ህንድ የሸሹት ለሳምንታት የቆየው ብርቱ ህዝባዊ ተቃውሞ ስልጣናቸውን እንዲለቁ ስላስገደዳቸው ነው።
ባለፈው ሀሙስ ጊዜያዊ መንግስቱን ለመምራት ቃለ መሀላ የፈጸሙት የኖቤል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሎሬት ሙሀመድ ዮኑስ፣ ምርጫ የማካሄድ ኃላፊነት ተጥሎባቸዋል።
ልጃቸው ሳጀብ ዋዘድ ጆይ ለታይምስ ኦፍ ኢንዲያ እንደተናገረው "ሁሲና ለአሁኑ ህንድ ነች። ጊዜያዊ አስተዳደሩ ምርጫ ለማድረግ በሚወስንበት ቅጽበት ወደ ባንግላዴሽ ትመለሳለች።"
የ76 አመቷ ሁሲና በምርጫ ለመወዳደር ስለመፈለጓ ልጃቸው ግልጽ አላደረገም። "እናቴ የአሁኑ የስልጣን ዘመን ሲጠናቀቅ ጡረታ የመውጣት ፍላጎት ነበራት" ብሏል ጆይ።
"እኔ ምንም የፖለቲካ ፍላጎት የለኝም። ነገርግን ባለፉት ጥቂት ቀናት በባንግላዴሽ እየተካሄዱ ያሉ ክስቶች የአመራር ክፍተት መኖሩን ያሳያሉ። ለፓርቲው ህልውና ስል ነው እየተናገርኩ ያለሁት" ብሏል በአሜሪካ የሚኖረው ጆይ።
የተማሪዎችን አመጽ ተከትሎ በተቋቋመው የጊዜያዊ አስተዳደር መንግስት ውስጥ ባንግላንጄሽን ከ15 አመታት በላይ የመራው የሁሲና አዋሚ ፓርቲ አልተወከለም። በሀገሪቱ በተቀሰቀሰው አመጽ 300 ሰዎች ተገድለዋል።
ሁሲና አሁን ላይ ህንድ ውስጥ ጥበቃ በሚደረግለት ቤት ውስጥ ይገኛሉ ተብሏል። የህንድ ሚዲያዎች ሁሲና በእንግሊዝ ጥገኝነት ለመጠየቅ መጠየቃቸውን ቢዘግቡም፣ የብሪቲሽ ሆም ኦፊስ ወይም የጥገኝነት ጉዳይ ቢሮ ያለው ነገር የለም።
የህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በጉዳዩ ዙሪያ ከእንግሊዝ አቻቸው ጋር ማውራታቸውን ቢገልጹም፣ ዝርዝር ጉዳዮቹን አላጋሩም።