ጠቅላይ ሚኒስትር ያባረሩት የባንግላንዴሽ ተማሪዎች ፓርላማው እንዲበተን ገደብ አስቀመጡ
ተማሪዎቹ ፓርላማው እንዲፈርስ ያቀረቡት ገደብ የማይጠበቅ ከሆነ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቆዋል
ሁሲና በቀረበባቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ምክንያት ኃላፊነታቸውን ለቀው ወደ ህንድ ለመሸሽ ተገደዋል
ጠቅላይ ሚኒስትር ያባረሩት የባንግላንዴሽ ተማሪዎች ፓርላማው እንዲበተን የሰአት ገደብ አስቀመጡ።
ጠቅላይ ሚኒስትር ሸኪ ሁሲና በተነሳባቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ምክንያት ኃላፊነታቸውን ለቀው ከሀገር ከኮበለሉ ከአንድ ቀን በኋላ ተቃውሞ እያደረጉ ያሉት የባንግላዲሽ ተማሪዎች ፓርላማው እንዲበተን ጠይቀዋል።
ተማሪዎቹ ፓርላማው እንዲፈርስ ያቀረቡት ገደብ የማይጠበቅ ከሆነ ጥብቅ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቆዋል።ቁልፍ ከሆኑት የተቃውሞ አስተባባሪዎች አንዱ የሆነው ናሂድ እስላም ከሌሎች ሁለት የተማሪ መሪዎች ጋር ሆኖ በፌስቡክ ገጹ ባስተላለፈው የቪዲዮ መልእክት ፓርላማው ማክሰኞ ከሰአት 9:00 ሰአት(0900ጂኤምቲ) መበተን አለበት፤ ይህ የማይሆን ከሆነ አብዮተኛ ተማሪዎች ዝግጁ እንዲሆኑ ጠይቋል።
የባንግላዴሽ ጦር ኢታማዦር ሹም ወከር-ሀዝ- ከተቀመጠው ገደብ ቀደም ብለው ስልጣን ከተረከበ በኋላ ምርጫ እንደሚያካሂድ ስለሚጠበቀው የጊዜያው መስንግስት አወቃቀር ጉዳይ ከተቃውሞ መሪ ተማሪዎች ጋር ይወያያሉ ተብሏል።
ተማሪዎቹ ይህን ገደብ ያስረቡት ከኢታማዦር ሹም ጋር ከተወያዩ ስለመሆኑ አልታወቀም።
ዘማን ለቀናት የቆየውን የተማሪዎች ተቃውም ተከትሎ ሁሲና ከኃላፊነት መልወቃቸውን ይፋ አድርገዋል። በሀገሪቱ ተቃውሞው የተነሳው መንግስት ያስተዋወቀውን የስራ ኮታ ስርአት በመቃወም የነበረ ቢሆንም ቀስበቀስ ሁሲና ከስልጣን ይወገዱ ወደሚል ጥያቄ ሊያድግ ችሏል።
ባንግላዲሽ በፈረንጆቹ 1971 ከፓኪስታን ነጻ ለመውጣት ካደረገችው የነጻነት ጦርነት ወዲህ አስከፊ በተባለው በዚህ አመጽ በመላ ሀገሪቱ 300 ገደማ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በሺዎች የሚቆጠሩ ደግሞ ቆስለዋል።
የተማሪ መሪዎች የኖቬል የሰላሜ ሽልማት አሸናፊ የሆኑት ሎሬት ሙሀመድ ዩኑስ የሽግግር መንግስቱ ዋና አማካሪ እንዲሆኑ እንደሚፈልጉ የተናገሩ ሲሆን የዩኑስ ቃል አቀባይም በተማሪዎቹ ፍላጎት መስማማታቸውን ገልጸዋል።
"እኛ እንዲሆን ከፈለግነው ውጭ የሚሆን መንግስት ተቀባይነት የለውም" ሲል በቪዲዮ መልእክት ያስተላለፈው እስላም "በጦሩ የሚደገፍ ወይም የሚመራ መንግስት አንቀበልም" ሲል አክሎ ገልጿል።
የ84ቱ ዩኑስ እና ግራሜን የተባለው ባንካቸው በሀገሪቱ የገጠር አካባቢዎች ለሚገኙ ድሃ ዜጎች ከ100 ዶላር በታች መነሻ በመስጠት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የባንግላዲሽ ዜጎችን ከድህነት ለማውጣት በሰሩት ስራ በ2006 የኖቬል የሰላም ሽልማት አሸናፊ ሆነዋል። ዩኑስ ባለፈው ሰኔ በማጭበርበር ተከሰው ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር። ዩኑስ የቀረበባቸውን ክስ አስተባብለዋል።
የባንግላዴሽ ተቃዋሚዎች ከደሀካ የሸሹት ሁሲና እንድታርፍ በፈቀደችው ህንድ ተናደዋል።
"ህንድ ምርጥ ወዳጃችን ነች...ህይወታችንን ያመሰቃቀለችውን ሰው በመደገፏ ህዝቡ በህንድ ተናዷል" ብለዋል ዩኑስ።
ህንድ ባንግላዴሹ ቀውስ ጉዳይ እየመከረች ነው ተብሏል።