የሃይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ምርት የቀነሰው በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚከሰቱ ደረቅ ሁኔታዎች ነው
አዲስ ዓለም አቀፍ ሪፖርት በ2023 የመጀመሪያ አጋማሽ የሃይድሮሊክ ኃይል ምርት ላይ ያለውን ታሪካዊ ውድቀት አረጋግጧል።
በታዳሽ ኃይል ምርምር ማዕከል የቀረበው ሪፖርት በአየር ንብረት ለውጥ ሳቢያ የሚከሰቱ ደረቅ ሁኔታዎች በሰኔ ወር በዓለም የውሃ ኃይል ምርት ላይ የ8.5 በመቶ ቅናሽ አስከትሏል ብሏል።
የሃይድሮ ኃይል ምርት መቀነስ ማለት በ2023 የመጀመሪያ አጋማሽ የዓለም የካርቦን ልቀቶች በትንሹ ጨምሯል ማለት ነው፤ ምንም እንኳን በአለም ላይ በጸሀይ እና በነፋስ ኃይል 12 በመቶ ቢጨምርም።
ሪፖርቱ ከዚህ ዓለም አቀፋዊ የምርት መቀነስ ውስጥ ሦስት አራተኛው የሚሆነው በቻይና ሲሆን በዚህ ዓመት መጀመሪያ ላይ ከፍተኛ የሙቀት መጠን አጋጥሟታል።
በጎርጎሮሳዊያኑ 2022 ክረምት እና በጸደይ 2023 መካከል አብዛኛዎቹ የደቡብ ምዕራብ ቻይና አካባቢዎች የዝናብ መጠን ያነሰ እና ከመደበኛው የበለጠ የሙቀት መጠን ታይቷል።
የአየር ንብረት ለውጥ በውሃ እምቅ አቅም ላይ የሚያስከትለው መዘዝ በመልክዓምድራዊ ሁኔታ ቢለያይም የዝናብ ሁኔታ ለውጥ እንዲሁም የትነት መጨመር እንደ ክልሉ ሁኔታ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ የውሃ ኃይል ምርት ላይ ተጽዕኖ ይኖረዋል።