ዓለም የምትጠቀምበትን ኤሌክትሪክ ከምን እያገኘች ነው?
ከሰል ዓለም ከምታገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ 35.4 በመቶ የሚሆነውን በመሸፈን ቀዳሚ ነው
የአለም የኢንነርጂ መረጃ በቅርቡ እንዳወጣው መረጃ ከሆነ በፈረንጆቹ 2022 ዓለም 29,165.2 ቴራዋት ሀወርስ ኤሌክትሪክ አመንጭታለች
የአለም የኢንነርጂ መረጃ በቅርቡ እንዳወጣው መረጃ ከሆነ በፈረንጆቹ 2022 ዓለም 29,165.2 ቴራዋት ሀወርስ ኤሌክትሪክ አመንጭታለች። መረጃው ይህ ከባለፈው አመት ጋር ሲነጻጸር የ 2.3 በመቶ ጭማሪ ማሳየቱን ጠቅሷል።
ከፍተኛው ኤሌክትሪክ የሚመነጨው ከምንድነው?
ከሰል ዓለም ከምታገኘው የኤሌክትሪክ ኃይል ውስጥ 35.4 በመቶ የሚሆነውን በመሸፈን ቀዳሚ ሲሆን የተፈጥሮ ጋዝ እና የውሃ ኃይል እንደቅደምተከተላቸው 22.7 በመቶ እና 14.9 በመቶ የሚሆነውን ይሸፍናሉ።
በዓለም ከከሰል ከሚመነጨው ኃይል ውስጥ 1/3 የሚሆነው በሶስት ሀገራት ጥቅም ላይ የሚውል ነው። ቻይና 53.3 በመቶ የሚሆነውን በመጠቀም ቀዳሚ ስትሆን ህንድ 13.6 በመቶ እና አሜሪካ 8.9 በመቶ በመጠቀም ይከተላሉ።
ለኤሌክትሪክ ኃይል፣ የብረት ፋብሪካ እና ለሲሚንቶ ፋብሪካ ጥቅም ላይ የሚውለው የድንጋይ ከሰል የዓለም ትልቁ የበካይ ጋዝ ልቀት ምንጭ ነው።ዓለም የምትጠቀምበትን ኤሌክትሪክ ከምን እያገኘች ነው?