በደቡባዊ ማዳጋስካር 1 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ተባለ
በሀገሪቱ 700ሺ የሚሆኑ ሰዎች እስካሁን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ አግኝተዋል
በማዳጋስካር ደቡባዊ ክፍል ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ ከድህነት ወለል በታች ይኖራል ተብሏል
በደቡባዊ ማዳጋስካር ከ1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ባለሙያዎች አስጠነቀቁ፡፡
በሀገሪቱ 700ሺ የሚሆኑ ሰዎች እስካሁን አስቸኳይ የምግብ እርዳታ እንደረሳቸውንና አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ከማልጋሲ መንግስት ጋር እየሰራ ያለውን የአለም የምግብ ፕሮግራምን ጠቅሶ ሲጊቲኤን ዘግቧል፡፡
የአለም የምግብ ፕሮግራም አሊስ ራህሞን በቂ እህል መሰብሰብ ባለመቻሉ ሰዎች የሚዘሩትና የሚሰበስቡት እህል እንደማይኖር ተናግረዋል፡፡
በማዳጋስካር "ጥልቅ ደቡብ" ክልል ውስጥ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ ከድህነት ወለል በታች ስለሚኖር ቤተሰቦችን እጅግ በጣም ተጋላጭ ያደርገዋል ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል ገልጿል።
በማዳጋስካር የዩኒሴፍ ምክትል ተወካይ ዣን ቤኖይት ማንሄስ "ሁሉም የረድኤት ድርጅቶች ይህ ቀውስ ወደ ረሃብ እንዳይቀየር በጋራ እየሰሩ ነው" ሲሉ ለአሶሼትድ ፕሬስ ተናግረዋል።
ነገር ግን ተጨማሪ ሀብት የሚፈልግ መበላሸት እያየን ነው ሲሉ ተናግሯል።
“ሀሳብ ልስጥህ በሀምሌ እና ነሐሴ ወራት 14,000 ህጻናት ለከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጦት የተጋለጡ ታክመዋል። ይህ አብዛኛውን ጊዜ በዓመት ውስጥ የምናስተናግደው ቁጥር ነው።” ብለዋል ዣን ቤኖይት ማንሄስ፡፡
ለአራት ተከታታይ አመታት የዘለቀው ድርቅ ሰብሎችን አጥቅቷል፣ በማዳጋስካር "ግራንድ ሱድ" ወይም በታላቋ ደቡብ የእርሻ ማህበረሰቦች የምግብ ክምችቶችን አሟጦታል ሲል ተናግሯል።
ደቡባዊ ማዳጋስካር ከግንቦት እስከ ጥቅምት በድርቅ የሚታወቅ ቢሆንም ዘንድሮ በጣም የከፋ ነው ተብሏል፡፡ በሀገሪቱ በልምድ ሩዝ፣በቆሎና ካሳቫ ማብቀል የሚጀመርበት ህዳር ወር፤ መሬቱ ደረቅ በመሆኑ ከባድ መሆኑ ተገልጿል፡፡