ከአንድ ወር በፊትም የፕሬዘዳንቱን የቀኝ እጅ ላይ የግድያ ሙከራ ተፈጽሞ ነበር
የማዳጋስካርን ፕሬዘዳንት ለመግደል የተወጠነውን እቅድ ማምከኑን የአገሪቱ መንግስት አስታውቋል።
እንደ አገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ገለጻ የውጭ ዜጎች ሳይቀር ተሳትፈውበታል የተባለውን የፕሬዘዳነት አንድሪ ራጆሊና የግድያ እቅድ መክኗል።
በዚህ ገድያ እጃቸው አለበት በሚል የተጠረጠሩ የውጭ እና የአገር ወስጥ ዜጎች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ፍራንስ 24 ዘግቧል።
የግድያ እቅዱ አላማው ፕሬዚዳንቱን ከመግደል ጀምሮ ሌሎች የማዳጋስካር የፖለቲካ አመራሮችን በማስወገድ የፖለቲካ ችግሮችን መፍጠር መሆኑን ዘገባው አክሏል።
ማዳጋስካር ከአንድ ወር በፊት የነጻነት በዓሏን ባከበረችበት ወቅት የፕሬዘዳንት አንድሪ የቀኝ እጅ በመባል የሚታወቁት ጀነራል ሪቻርድ ራቫሎማናን የመግደል ተሞክሮ እንደከሸፈ ዘገባው በተውስታ ጠቁሟል።
የአሁኑ የማዳጋስካር ፕሬዘዳንት አንድሪ ራጆሊና ከሁለት ዓመት በፊት በምርጫ አሸንፈው ወደ ስልጣን የመጡት።
የ44 ዓመቱ ፕሬዚዳንት አንድሪ በፈረንጆቹ 2009 በአገሪቱ ወታደር ታግዘው እስከ ፈረንጆቹ 2014 ድረስ ጊዜያዊ የሽግግር መንግስት ፕሬዚዳንት ሆነው አገልግለውም ነበር።
27 ሚሊዮን ህዝብ ብዛት ያላት ደቡበ አፈሪካዊታ አገር ከፈረንሳይ ቅኝ ግዛት በፈረንጆቹ 1960 ዓመት ነጻነቷን ከተቀዳጀች በኋላ የቀድሞዋ ማላጋሲ ሪፐብሊክ ስሟን ወደ ማዳጋስካር ቀይራለች።